• Sat. Apr 4th, 2026

በጦር ሜዳ ጀግናውን ኦነሰ መቋቋም የተሳነው የፋሺስቱ ብልፅግና ሰራዊት ቁጭቱን ለመወጣት ወደ ሰሜን እና ምዕራብ ሸገር ዞኖች፣ የገጠር መንደሮች አፈ ሙዙን አዙሮ ለሰርጓ ሁለት ቀን ብቻ የቀራት ቃሬ እና የሌሎችንም ህይወት ቀጥፏል

Jun 3, 2024

ግንቦት 29፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኢምፓየሪትዋ መፈረካከስ እና ያላቸው ቁመና የኦሮሞ ነፃነት ኃይልን መቋቋም እንደማይችል የተገነዘበው የፋሺስቱ ብልፅግና ሰራዊት የጦር ሜዳ መሳሪያዎቹን በሰሜን ሸገር ሰላሌ ዞን፣ ጃርሶ ወረዳ እና በምዕራብ ሸገር ዞን፣ ጀልዱ ወረዳ ላይ አፈሙዙን ወደ ሰላማዊ ሕዝብ በመቀሰር በሕይወትና ብንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። የተጠቀማቸው መሳሪያዎችም ሞርታርና ዙ-23 (Z-23) እንደሚጨምር የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልፀዋል። ይህን አይነት አረመኔያዊ አድራጎት ከሁለት ሳምንት በፊት በጉጂ ገጠሮች ፈፅመውም ነበር።

አድራጎታቸውም በግልፅ የታየው ሚያዚያ 20፣ 2024 በምዕራብ ሸገር ዞን፣ ጀልዱ ወረዳ፣ ጎጆ ከተማ ውስጥ የጦር መሳሪያውን በማቆም ወደ ገጠር ቀበሌዎች በማስወንጨፍ በሰው ሕይወትና በከብቶች ላይ ጉዳት ማድረሱንም ነው። 

ይኸውም ከሁለት ቀን በኋላ የሰርግ ቀንዋን ለማየት በጉጉት ላይ የነበረችውን እና የአሶሌ ቀበሌ ነዋሪ የነበረችው ቃሬ አበራሽ በቀለ በደረሰባት ከባድ ጉዳት በአምቦ ሆስፒታል ህክምና ቢሰጣትም ህይወትዋን ማትረፍ አልቻሉም። 

የፋሺስት ብልፅግና የጦር ወንጀል በቀጥታ ወደ ሚዲያ እንዳይወጣ የስልክም ሆነ ማንኛውንም የሚዲያ መስመር ማገዱን ቀጥለዋል። በዚህም ምክንያት የኦሮሞ ሕዝብ እውነታ አይደለም የአለም ሕዝብ ሊሰማ በአካቢውም ያሉ ነዋሪዎች ዝርዝር ሁኔታውን ለማወቅ ከባድ ሆኖባቸዋል። 

ስለዚህም በሰሜን ሸገር ሰላሌ ዞን፣ በወረ ጃርሶ ወረዳ ውስጥ ወደ ገጠር ቀበሌዎች በሚተኮሰው ከባድ መሳሪያ የሰው ሕይወት ማለፉንና ንብረቶችም መውደማቸው ቢሰማም የሞቱትንም ሆነ የተከሰተውን ጉዳት ዝርዝር ማቅረብ አልተቻለም።

ኦሮሞ ይህንን አሸባሪ ስርዓት ከሕዝባችን ጫንቃ አርግፈን ለማሽቀንጠር አንድነት ይኑረን። 

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading