• Wed. Nov 25th, 2026

የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የኦሮሞ ነጻነት ጦር በኢርቡ ሽኒጋ ዘመቻ ጠላት ላይ በወሰደው እርምጃ በሞት እና በማቁሰል ቀጣ

Jun 3, 2024

ሰኔ 1፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) 

የኦሮሞ ህዝብ ክንድ እና ጋሻ የሆነው የኦነሰ በደቡብ ምስራቅ ዞን፣ የጃል ነdhii ገመዳ ብርጌድ በምስራቅ ሸገር አዳሚ ቱሉ እና ጂዶ ኮምቦልቻ የኢርቡ ሽኒጋን ዘመቻ ለማሳካት በወሰደው እርምጃ የጠላትን ሃይል ትንፋሽ በማሳጣት ሲያሳድደው ውሎዋል።

ግንቦት 29፣ 2024 በአዳሚ ቱሉ እና ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ፣ በአነኖ-ሺሾ ቀበሌ ፊንፊኔን እና ሻሸመኔን በሚያገናኛው ዋናው መንገድ ላይ የኦነሰ ከምሽቱ 5:10 እስከ ሌሊት 6:40 በወሰደው የደፈጣ እርምጃ በእግር እና በኦራል ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የፋሺስቱን የብልጽግና ሰራዊት በሞት እና በማቁሰል ሲቀጣ ከሞትና ከመቁሰል የተረፉትም እግሬ አውጭኝ ብለው በተለያየ አቅጣጫ ፈርጥጠዋል።

ከጠላት ሃይል የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በዕለቱ ሌሊት ላይ ተጨማሪ ረዳት ኃይል እንዲላክላቸው ለበላይ አመራር ቢደውሉም ተጨማሪ ኃይል ባለማግኘታቸው በጊዜ ህክምና ቢያገኙ መዳን የሚችሉ ቁስለኞቻቸው ሞተዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሚውስደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

#የኢርቡ_ሺኒጋ_ዘመቻ

ድል ለኦሮሞ ህዝብ እና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply