• Sat. Mar 14th, 2026

በምሥራቅና ምዕራብ አርሲ ዞኖች የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ፣ ማሰር፣ ማሰቃየት፣ መግደል፣ በጅምላ ገድሎም ወደ ገደል ከመወርወርም በላይ መናገር እና መስማት የማይችልን ቄሮ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባል ነው በማለት ገድለዋል

Jun 4, 2024

ግንቦት 4፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በፋሺስት አብይ አህመድ አገዛዝ ጨካኞች ሁሉ መሳሪያ የማንገብ መብት አላቸው። ስለዚህም ሚሊሻዎችንም ጨምሮ ምንም አይነት የመሳሪያን አጠቃቀም መብት እና ግዴታን ሳያስተምሩ ኦሮሞ የሆነ ሁሉ ብልፅግናን እስካልደገፈ ድረስ በጠላትነት በመፈረጅ ሰብዓዊነት በጎደለው መልኩ የህዝብን የመኖር ህልውና እየነፈጉ ይገኛል። 

ምሥራቅ አርሲ ዞን 

ጀጁ ወረዳ

ግንቦት 4፣ 2024 በሁሩታ ዶሬ ቀበሌ፣ ዲልዲላ ጃራ በተባለ መንደር የሚኖሩትን የሀገር ሽማግሌ ኦቦ ጃራ Dhuጎ የተባሉ ሰው አንድ የስረዓቱ ሚሊሻ በብሄሩ አማራ የሆነ በቤታቸው ገብቶ በጩቤ ወግቷቸው የሞቱ መስሎት ከሄደ በኃላ ቤተሰባቸው ሀኪም ቤት ለህክምና እንደወስዷቸው ለአቢኦ ተናገሩ።

ኦቦ ጃራ Dhuጎ በህብረተሰቡ የተወደዱና የተከበሩም ናቸው። የደረሰባቸው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ቤተስብ ሃዘን ተሰምቶታል። የአካባቢውም ሕዝብ “ፅንፈኛ አማሮች ወደ አባት ሐገራችን መጥተው እየኖሩም እኛን መግደላቸው በጣም ያሳስበናል” በማለት ገልፀዋል።

የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር ቡድን ሚያዚያ 15፣ 2024 ሳቄ ቦኪቻ ቀበሌ ውስጥ ነዋሪዎችን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትረዳላችሁ በሚል የሃሰት ውንጀላ ብዙ መኖሪያ ቤቶችን ከሙሉ ንብረት ጋር በእሳት አጋይተዋል። ከተቃጠለባቸውም ንፁሃን ኦሮሞዎች መካከል ስማቸውን አቢኦ ከምንጮቹ ያገኘው የሚከተሉት ናቸው፦

  1. ሃጂ አብዱላሂ ቃድር፣
  2. ከድር ሃጂ አብዲ፣
  3. ኡስማኢ ሃጂ አብዱቃድር፣  
  4. ጀሜ አብዱላሂ፣   
  5. ሼክ ሁሴን ኢስማኢል እና
  6. ምሳ አሊዪ ሲሆኑ፣ ቤት እና ንብረት የወደመባቸው ሁሉ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከባድ ችግር ሌይ እንዳሉም አክለው ገልፀዋል

ከዚሁ ወረዳ ሳንወጣ በሁሩታ ቀበሌ የጁስ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን ታጣቂዎች እንደ እስር ቤት እየተጠቀሙ ሲሆን እስረኞቹም ከተለያየ የኦሮሚያ አካባቢ የተያዙም እንደሆኑ ታውቆዋል። እነዚህም እስረኞች በጅምላ በተለያየ ግዜ ግድያ እንደሚፈፅሙባቸው የአቢኦ ምንጮች ተናግረዋል። 

በዚህም መሰረት ሚያዚያ 2፣ 2024 እነዚህ የብልፅግና ቡድን ታጣቂዎች በቁጥር 33 ሰዎችን በመያዝ በግቢው ውስጥ ካቆዪ በኃላ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ ስድስት ሰዎችን ሌሊት ላይ አውጥተው ገድለው ወደ አዋሽ ወንዝ እንደወረወሯቸውም ምንጮቻችን አክለው ገልፀውልናል። ከተገደሉት ሰዎች መሃክል ከስሬ ወረዳ፣ ኮሎባ ሀዋስ ቀበሌ ነዋሪ እንደሚገኝበት እና አንዲት ቃሬ የትውልድ ቦታዋ ያልታወቀም እንዳለችበት ተናግረዋል። የአካባቢው ሕብረተሰብ ከተገደሉ በሁለተኛው ቀን አስከሬናቸውን ሰብስበው እንደቀበሩም ገልፀዋል።

ሮቤ ዲዳ ወረዳ 

በፓለቲካ ውስጥ ምንም ዓይነት ተሳትፎ የሌላቸውን በመራሮ ሲቤ ቀበሌ ከሁለት ቀን በፊት ጆሮው መስማትም መናገርም የማይችልን ወጣት አቡሽ ቃሶ የተባለን በጥይት ደብደበው መግደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።

ቄሮ አቢሹ ቃሶ መስማትም ሆነ መናገር የማይችል ሲሆን አረመኔውና ፋሺስቱ የብልፅግና ቡድን ጦር ሚያዝያ 21፣ 2024 በጥይት ደብደበው ከገደሉት በኋላ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባልን ገደልን በማለት ለህዝብ እንደ ትርዒት ስያሳዩት እንደዋሉ የሚያውቁት ሰዎች ለአቢኦ ገልፀዋል።

መርቲ ወረዳ 

በወተሮ ዲኖ ቀበሌ እና አረዳ ላላ ቀበሌ የፋሽስቱ የብልፅግና ቡድን ሰራዊት የህዝብ ንብረት ዘረፋውን አጠጡፎ ቀጥሏል።  

ለዚህም ዘረፋ በወተሮ ዲኖ ቀበሌ ኢላላ መንድር ውስጥ ሚያዚያ 15፣ 2024 ሰለባ የሆኑት በከፊሉ ስማቸውን ያገኘነው፦

  1. አርባ ሸምሱ፣
  2. ጣኣ ዳdhi፣ 
  3. አርፋ ሙክታር፣
  4. ሙራዶ ጉቶ፣
  5. በሻ ጎዳና እና
  6. ቃሲሞ ሃጂ ሲሆኑ ከእነርሱም 45 ፍየሎች እና እቤታቸው ውስጥ ያገኙትን እቃዎች ሁሉ እንደዘረፉዋቸው የእካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል። 

በዚሁ ቀበሌ ውስጥ አርዳ ካምፕ በመባል በሚታወቀው ሥፍራ አባቡ ጀማሎ እና ኩሮ ገለቶ የሚባሉትን ግለሰቦች ከባድ ድብደባ ከፈጸሙባቸው በኋላ ንብርታቸውንም ዘርፈው፣ ከዘረፍዋቸውም መሃከል 11 ፍየሎች እና 2 በሬዎችን በአካባቢው አርደው እንደበሉም ምንጮቻችን ነግረውናል።  

ምዕራብ አርሲ ዞን 

ዶዶላ ወረዳ

የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን የኦሮሞን ሕዝብ በጠመንጃ አፈሙዝ ሰብረን ኢምፓየሪቱን መልሰን እናቋቁማለን የሚለው የብልፅግናው ቡድን አረመኔያዊ ስራውን አስፋፍቶ ቀጥሏል። ይኸውም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባሎችን ቤተሰብ ቀዬ በማቃጠል እና ለህዝባቸው ተቆርቋሪነት ያላቸውና በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነት አላቸው ብለው የሚጠረጥሩዋቸውን ሰዎች በማሰር፣ እስር ቤት ውስጥ በማሰቃየት፣ በመዝረፍ እና በመግደል ላይ ይገኛሉ። 

ይህንንም እኩይ ተግባር የሚመሩት እና ትእዛዝ የሚያስተላልፉት የቡሬ አዶሌ ቀብሌ አስተዳዳሪ ጫላ ኢርኮ እና የብልፅግና ፓርቲ ተጠሪ አወል ሁንዲሳ ናቸው።

አዳባ ወረዳ

ንፁሃን ኦሮሞዎች በሃሰት ዉንጀላ ከተለያዩ አካባቢዎች ተይዘው ወደ ወረዳው ካመጧቸው በኋላ በድብቅ በጅምላ ተገድለው ገደል ውስጥ እየተጣሉ መሆኑን አቢኦ ከምንጮቹ አረጋግጧል። እነዚህንም ሰዎች ማንነታቸውን ለማወቅ ከባድ እንደሆነባቸውም ገልፀውልናል። 

ገደብ ሀሳሳ ወረዳ

የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር ቡድን የሕዝብ የበዓል ቀን ምን ማለት እንደሆነ የማይገባቸው የደናቁርት እና አረመኔ ስብስብ መሆናቸውን የዕለት ዕለት ተግባራቸው ያሳያል። ስለዚህም ሚያዚያ 10፣ 2024 የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትደግፋላችሁ በሚል ስም፦

  1. ኦቦ አብዱሌ ጃርሶ ጂሎ ከጮፊራ ሻሼ ቀበሌ እና 
  2. ኦቦ ጂብሪል ከኒሶ ከጮፊራ ሁሉቆ ቀበሌ በአሰቃቂ መንገድ ገድለውም አልረኩም።

ስለዚህም በዚሁ ዕለት የኢድ በአል በተከበረበት ቦታ ኦቦ ጅብሪል ክኒሶ የትባሉትንም ገድለው ጥለዋቸው እንደሄዱም ምንጮቻችን ዘግበውልናል።  

#የሽኒጋ_ቃልኪዳን_ዘመቻ

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚወስደው እርምጃ እስከ ነፃነት እና ኦሮሚያ ሉዓላዊ ሐገርነትዋን እስከምትጎናፀፍ ይቀጥላል!

ድል ለኦሮሞ ሕዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading