• Sat. Mar 14th, 2026

የኢርቡ ሺኒጋ ዘመቻ እና ጭንቀት ውስጥ የገባው የብልጽግና ስርዓት ==================

Jun 7, 2024

ታንኩን እና ባንኩን ይዞ የሚያቅራራው ቡድን፣ለልማት ሊውል የሚገባን 10 ቢሊዮን ብር ለጦርነት ማዋሉን በድፍረት የሚያወራው፣ ችግሩ ራሱ ሆኖ ሳለ ችግር ፈቺ ለመምሰል የሚጥረው፣ ራሱ በድሎ፣ ራሱ ገሎ፣ ራሱ አስሮ፣ ራሱ አፈናቅሎ ሲያበቃ ያላንዳች ሀፍረት ብቸኛ የፍትህ ምንጭ መስሎ ለመቅረብ ፈትለፊትህ  የሚቆም ፍጹም ጨካኝ ቡድን ነው። 

የሂትለር በጌስታፖው (Gestapo) ፣ ስታሊን በጉለን (Gullen) በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸውን እንደ ፈጁ ሁሉ፣ አብይ አህመድም ባቋቋመው ኮሬ ነጌኛ እና በመከላከያ ሰራዊቱ ሚሊዮኖችን ፈጅቶአል። ይሁን እንጂ የግድያው መብዛት፣ የእስራትና ዝርፈያው መጠናከር፣የስደት እና ከቄዬ ማፈናቀል ድርጊቶች ህዝቡ ፈርቶ እና ተስፋ ቆርጦ ትግሉን ትቶ ለስረዓቱ እንዲገዛ ሆን ተብሎ የተደረገ ቢሆንም የታሰበው ሰላም ጠፋ፣ ህዝቡም እንቢኝ፣ አሻፈረኝ አለ፣ትግሉም ተቀጣጠለ። በኢምፓየሯ የተፈጠረው ችግር ከባድ ስለሆነ ኢኮኖሚው ወደቀ፣ የምዕራባውያን እርዳታ እና ብድር ሲቀዛቀዝበት ያለው አንድ እድል ሀገራዊ ምክክር ብሎ መጮኽ አጀንዳው አደረገ።  ግራ የገባው……እንደሚባለው ብልጽግና ከዚህ ጦርነት ለመውጣት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወታደሮችን የገብረ ሲሆን ወደፊትም ሚሊዮኖችን ለመገበር ወደ ኋላ አይልም። ከባድ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶአል። የሚያመነጨው የመፍትሄ ሃሳብም የለውም። ከባድ ቅርቃር ውስጥ የገባው ብልጽግና የነገ ህልውናው ጥያቄ ውስጥ ገብቶአል። 

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቁ ችግር የዲሞክራሲ መጥፋት እና የፖለቲካ ሜዳው ዝግ መሆኑ እንደሆነ አብዛኞቹ የፖለቲካ ስዎች ያነሳሉ። እንድያውም ለተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በሩ ዝግ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገልፃሉ። 

የፖለተካ ሙሁሩ እና የKFO የፖለቲካ ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያን ጉዳያ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልህክተኛ ለሆኑት Mr.Mayik Hammer እንደገለፁት የሀገሪቱ ችግር ዲሞክራሲን አለመለማመድ እንደሆነ ገልጸውላቸዋል። 

እውነተኛ ዲሞክራሲ እንዳይኖር እና ሀገሪቷ ወደዚህ አስከፊ ሁኔታ እንድትገባ የገዢው መንግሰት ድርሻ ከፍተኛውን ቦታ እንደሚይዝ አክለዋል። ይባስ ብሎ  ኢትዮጵያን እያስተዳደርኩ ነው የሚለው ይህ ቡድን በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን የሚሉትን አካላት ቢሮአቸውን በመዝጋት፣አመራሮቻቸውን አሳዶ በመግደል፣ ቢሮዎቻቸውን በመዝጋት መፈናፈኛ እንዲያጡ በመደረጋቸው የሆኔታው አስገዳጅነት ወጣቶች ሳይወዱ ወደ ትጥቅ ትግል እንደገቡ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። የኦሮሞ ነጻነት ስራዊትም በዚሁ ምክንያት ነው መሳሪያውን አጥብቆ የያዘው ብለዋል ፕሮፌሰሩ። 

ፋሽስቱ የpp ቡድን “የሌባ ዓይነ ደረቅ….” እንዲሉ በኢምፓየሯ ውስጥ የሰላማዊ ትግል በር ክፍት እንደሆነ፣ ማንም የፈለገዉን ድርጅት የመደገፍ መብት እንዳለውና ተቃዋሚዎች በዲሞክራሲያዊ መንገድ የመንቀሳቀስ መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ በተለያዩ ጊዜያት ሲናገር ቢደመጥም እውነታው ግን ተቃራኒው ነው። ለአብነትም የKFOነ እና የABO ፓርቲ አመራሮችን ማሰሩ አንዱ ማሳያ ሲሆን በተጨማሪም ጃል በቴ ሁርጌሳ ላይ ስርዓቱ የፈጸመው ግድያ አጥጋቢ ማስረጃ ነው።

በዚህ ሁኔታ ባለፈዉ ሃሙስ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በትጥቅ ትግል ለሚታገሉት አካላት ባደረጉት የሰላም ጥሪ የሰላም በሩ ክፍት እንደ ሆነ ተናግረዉ ነበር። ነገር ግን ክፍት ለመሆኑ የሰጡት ማስታማመኛ በንግግራቸው ዉስጥ አልተደመጠም። የተከፈተ የሰላም በር ካለመኖሩም በላይ ንግግሩ ሆን ተብሎ ህዝብን ለማሞኘት ታስቦ የተለፈለፈ ማደንቆርያ ለመሆኑ ጥርጥር የለንም። 

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ ንግግሩ ”የራስን መብት በመሳሪያ ጫካ ውስጥ የምንፈልግበት ጊዜ ላይ አይደለንም” በማለት ያለውን ስጋት ሲገልጽ ”ሰላም፣ ሰላም፣ አሁንም ሰላም የምንለው ለማስመሰል ወይም እንደ ገደል ማሚቱ ለመደጋገም አደለም” በማለት ተማጽኖአል። 

በመሬት ላይ ያለው ተጨባጭ እውነት ግን የኦሮሞ ህዘብ በEPRF/TPLF ስርዓት የበለጠ አስከፊ ጭቆና ውስጥ መሆኑን ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ህዘቡ ይናገራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ብዙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በEPRF/TPLF አስተዳደር ዘመን በትንሹም ቢሆን የ ዲሞክራሲ ጭላንጭል የነበረ ቢሆንም  በአሁኑ ከነጭራሹም ጠፍቶ አምባገነናዊነት  እየተንሰራፋ መሆኑን ይናገራሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የብልጽግናው ቡድን  በተለያዩ ጊዜያት በውሽት እርቅ እና ምክክር ሸፋፍኖ በሀገሪቱ ዉስጥ የሚገኙትን ብሔረ ሰቦች በአንድ ቅርጫት ጨምሮ ለመጓዝ እየሞከረ መሆኑ ግልጽ ነው። አንድን ሀገራዊ ምክክር ሙሉ ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ አሳታፊነት ሲሆን የዚህ ቁልፍ መለክያ አለመኖር ምክክሩ የይስሙላ ምክክር መሆኑ ግልጽ ሆኖ በመታየቱ ስርዓቱ ከባድ ድንጋጤ ውስጥ መግባቱን ታዛቢዎች በግልፅ መናገራቸው ታወቆአል።

ብልጽግና በተለያዩ ጊዜ እርቅ እና ሰላም እንዳይመጣ ሲያደናቅፍ ነበር። በሃገራዊ  ምክክር ኮሚሽኑ ስር ተደብቆ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም ሙከራ ላይ መሆኑ እሙን ነው።

በዚው ሰሞን ABO ከህግ ውጪ ታሰሩበት ከፍተኛ አመራሮቹ አሳሳቢ ሁኔታ በተለያዩ ጊዜያት የሀገራዊ ምርጫ ቦርድን በመጠየቁ ምርጫ ቦርድም በበኩሉ ጥያቄውን ለኢምፓየሯ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረብ  ተወርቶዋል።

ከጃል በቴ ግድያ በኋላ በኢምፓየሯ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው ABO ከዚህ ቀደም የታሰሩት ከፍተኛ አመራሮች ያሉበትን ሁኔታ ብዙ ጊዜ ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ ሲያቀርብ ነበር። ይሁን እንጂ የብልጽግናው ቡድን ተቃዋሚዎችን መግፋቱን የፖለቲካ አዋቂዎች ይናገራሉ።

ጠንካሮቹን የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክሩ መቅረት እና በትጥቅ ትግል ከሚታገሉት እንደነ ABO-WBO ከምክክሩ ውጪ አድርጎ በኢምፓየሪቷ የሚካሄደው ምክክር ትርጉም ስለማይኖረው፣የብልጽግናው ቡድን ስልጣኑ ላይ ለመቆየት እያታለለ ተቀባይነትን ለማግኘት እየሰራ ይገኛል።

ብልጽግና ስለ ሀገራዊ ምክክሩ እያወራ ህዝቡን ለማታለል በሚፈልግበት እና የተለያዩ አካላትን ወደ ሚዲያው እያወጣ ፕሮፖጋንዳ በሚነፋበት ወቅት ABO-WBO የኢርቡ ሺኒጋ ዘመቻ አውጆ የብልጽግናን ጦር አብዛኛውን ገሎ ሌሎቹን በማቁሰል በቁጥር እና በዓይነቱ ብዙ የሆነ የጦር መሳሪያ በመማረኩ ብልጽግናን አስደንብሮት ይገኛል።

WBO ባሳየው አስገራሚ ዘመቻ እና አንድነት እንዲሁም WBO ውስጥ ያለውን ከፍተኛ መናበብ በብልጽግና ውስጥ ከፍተኘ ድንጋጤ ፈጥሮዋል። ኦሮሚያ ውሰጥ የሚካሄደውን ድርጊቶቸ በመረዳት የኦሮሚያው ብልጽግና መግለጫ፣ የሚንስተሮች ምክር ቤት፣ፓርላማ እና የማስመሰል ንግግር የሚናገሩት ባለስልጣናት፣ የብልጽግናን ድጋፍ ፍለጋ መሆኑን ከንግግራቸው መረዳት ይቻላል። እንዲያውም WBO  በኢርቡ ሺኒጋ ዘመቻ እየወሰደ ያለው እርምጃ ይበልጥ እንዳሳሰባቸው መረዳት ይቻላል።

የኢትዮጵያ ኢምፓየር መፍረስ እንጂ ተጠግና የምታመጣው መፍትሄ የለም።ስለዚህ በጠመንጃ አፈሙዝ የተመሰረተችውን ኢምፓየር በጠመነጃ አፈሙዝ አፍርሰን፣ ነጻ ኦሮሚያን ለመመስረት ከWBO ጎን በመቆም PPን ከስሯ እንንቀል የመጨረሻ መልህክቴ ነው።

ሆራ ቡላ!

ድል ለኦሮሞ ህዝብ

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading