• Tue. Nov 24th, 2026

ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሺኒጋው የቃለኪዳን ዘመቻ በሰሜንና በምዕራብ ሸገር ዞኖች በርካታ ቦታዎች ላይ በብልፅግና ሰራዊት ላይ የማጥቃት እርምጃ በመውሰድ ድል አስመዝግቧል

Jun 22, 2024

ሰኔ 21፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) 

የኦሮሞን ህዝብ አደራ ተሸክሞ ምንም ሳያጓድል ከግብ ለማድረስ ከጨቋኝ፣ ከዘራፊ እና ከአረመኔው ቅኝ ገዢ ቡድን ለማላቀቅ ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የማያዳግም እርምጃውን ቀጥሏል። ጠላት የሆነችው ኢምፓየሪትዋ፣ አገዛዝዋን በሃገሩ በኦሮሚያ ላይ ለማስቀጠል አረመኔያዊ ድርጊቶችን የሚያከናውኑላትን ቡድኖች በማሰማራት የኦሮሞን ህዝብ መዝረፍ፣ ክፉኛ ድብደባን ማካሄድ፣ ማሰርና ማሰቃየት፣ መግደል፣ ቤቱን ከነንብረቱ በላዩ ላይ በማቃጠል እና በማፈናቀል እያሰቃየች ቢሆንም ለአንዴና ለመጨረሻ ከእነ ሰንኮፍዋ እነቀላታለሁ ብሎ በተነሳሳው መሰረት በጀግንነት በሚወስደው እርምጃዎች ጠላትን በመደምሰስ መና እያስቀረ ይገኛል።

በተለይ በአዲስ መልክ የተጀመረው የሽኒጋው ቃል-ኪዳን ዘመቻ በመላው ኦሮሚያ በፋሽስቱ ስራዊት ላይ ከግንቦት 28፣ 2024 ጀምሮ ድል እያስመዘገበ ይገኛል።

የኦነሰ ማዕከላዊ ዞን በሰሜን ሸገር ዞን፥ በሂdhaቡ አቦቴ፣ በደገም፣ በያያ ጉለሌ፣ በሙከ ጡሪ፣ ሜታ ሮቤ እና አቡና ግንደበረት ወረዳዎች የኦሮሞን ህዝብ ከቤቱ መውጣትና መግባት ከልክሎ የነበረውን የጠላት ጦር ላይ የጥቃት እርምጃ በመክፈት ጠላትን እያሯሯጠ ግማሹን ሲገድል፣ ግማሹን በማቁሰል እና አንድ 50 አለቃቸውንም በመማረክ ድሉንም ሁለት ጠላት ሲጠቀምበት የነበረን ፓትሮል ከጥቅም ውጪ በማድረግ አጠናቋል።

በሂdhaቡ አቦቴ ወረዳ 

ጀግናው የኦነሰ ሰኔ 12፣ 2024 ወደ ድሬ ባንቱ ቀበሌ የገጠር መንደሮች የህዝቡን ከብቶች ለመዝረፍ ተሰማርተው በነበሩ የብልፅግና ሚሊሻዎችና የጦር ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ ሁለት ወታደሮችን ወዲያው ሲገድል የተረፉትም ቁስለኞቻቸውን ይዘው አካባቢውን ለቅቀው ወደ መጡበት እንዲመለሱ በማድረግ የማጥቃት እርምጃውን በድል ቋጭቶዋል።

ደገም ወረዳ 

ቦሶና ሌኒ በተባለ ሥፍራ ሰኔ 12፣ 2024 ከሰዓት በኋላ 10 ሰዓት ላይ በሁለት ፓትሮልና በእግር ሲጓዝ የነበረን የጠላት ኃይል፣ ጀግናው ኦነሰ በመክበብ ሁለቱም ፓትሮሎች ላይ የንበሩትን ከነመኪናቸው ጋር ከጥቅም ውጪ ከማድረጉም በላይ በእግር ሲጓዙ የነበሩትንም የሚገባቸውን አይምሬውን ቅጣት አግኝተው ክፉኛ ከቆሰሉትና ሆስፕታል ከገቡት መሃከልም ሁለቱ እዚያው ከደረሱ በኃላ መሞታቸው ተስምቷል።

ያያ ጉለሌ ወረዳ

በዳዴ ዱፍቱ ቀበሌ ሰኔ 11፣ 2024 የኦነሰ በወሰደው እርምጃ 7ቱን ወዲያው ሲገል ግማሹን በማቁሰል ቀጥቷቸዋል።

ሙከ ጡሪ ወረዳ

ሰኔ 11፣ 2024 የብልፅግናው ሰራዊት ቡድን በሱሉልታና በሙከ ጡሪ መካከል በፓትሮል ሲጓዝ የነበረን የጠላት ሃይል ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በመክበብ እብዛኞቹን ከአፈር ሲቀላቅል አንድ የ50 አለቃንም በመማረክ አኩሪ ድል አስመዝግቧል።

ሜታ ሮቢ ወረዳ

ሰኔ 6፣ 2024 በDhiሴ ኤላ ቀበሌ ውስጥ ህዝቡን ለመግደል እና ለመዝረፍ በሶስት መኪና የተሰማራውን የብልፅግና መንግስት ጦር ከበባ ውስጥ አስገብቶ በመምታት አንድ ፓትሮል መኪና አመድ አድርጎ ስምንት የብልፅግና ወታደሮችን በመግደል አምስቱን ማቁሰሉን የመካከለኛው ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለአቢኦ አሳውቆዋል።

አቡና ግንደበረት ወረዳ

የኦነሰ በጋጎ ኦስሌ ቀበሌ ውስጥ ሰኔ 6፣ 2024 በስብሰባ ስም ህዝብ እያሸበረ የነበረውን የብልፅግና ጦር በመክበብ ያቀደውን የሽብር ተግባር ሳይፈፅም ወደኃላ በማፈግፈግ ወደ መጣበት ከተማ እንዲሸሽ ተገድዶዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply