• Mon. Mar 16th, 2026

የምሥራቅ ዞን የኦሮም ነፃነት ሰራዊት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ ውስጥ በወሰደው እርምጃ ጠላትን ሙትና ቁስለኛ አድርጓል

Jun 28, 2024

ሰኔ 26፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ በጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ፣ ጫላ ገላ ሁሎ ቀበሌ በሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ መሰረት በፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ላይ ሰኔ 18፣ 2024 ከጠዋት 12:00 እስከ 3:00 ሰዓት ድረስ በወሰደው የማጥቃት እርምጃ 10 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ ከ15 በላይ አቁስሏል።

ይህንንም ጀግንነት እና አይበገሬ ኃይሉን ለጠላት ያሳየው ከአንድ ቀን በፊት ማለትም ሰኔ 17፣ 2024 በነበረው ጦርነት የጠላት ኃይል ቁስለኛውን ሳያነሳ በመፈረጠጡ፣ ለመርዳት እና ሬሳቸውንም ለመውሰድ፣ እንዲሁም የኦንሰን ለማጥቃት የበለጠ ኃይል አደራጅቶ በአራት አቅጣጫ ለመጣው ሃይል ነው። 

ይህ የፋሺስት ብልፅግና ቡድን ጦር በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ኃይሉን ለማጠናከር እየጣረም ይገኛል። ለዚሁ የማጠናከር ስልት ብሎ የወሰደው የአርጎባን ብሔረሰብ፣ የሶማሌ እና አፋር ክልሎች አዋሽ ካምፕን ጨምሮ ከራሱ ጦር ጋር ቀላቅሎ በሁለት አቅጣጫ ወደ ቦርደዴ ከተማ እና አንጫራ ወረዳ ጨለለቃ ከተማ ዘመቻ ቢከፍትም አንበሳው የኦነሰ አክሽፎበታል።

#የሽኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading