ሰኔ 30፣ 2024 አራት ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ኢምፓየሪትዋ ከተመሰረተችበት ዘመን ጀምሮ የንፁሃን ኦሮሞ ልጆች ደም በገዢዎችዋ እጅና በታዛዦቹ እየፈሰሰ ሲግኝ በፋሺስቱ የብልፅግና ቡድን ደግሞ በአሰቃቂ መንገድ ገድለው ከመጣልም በላይ ከገደልዋቸው በኋላም በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ እና ዳdhii ገላን እንዲሁም ሞይቦን በቀላ ላይ የሞከሩትን ድራማ ዛሬ ደግሞ የጃል በቴ ኡርጌሳን ወንድም እና ዘመዶቹን ለመድገም አስረው እያሰቃዩዋቸው ነው።
በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚገኘው የኦሮሞ ትውልድ አሻፈርኝ ብሎ ኢምፓየሪትዋን ከመሰረትዋ ፈንቅሎ ለመጣል በ11ኛው ሰዓት ላይ ይገኛል። ይህንን ትዉልድ በገንዘብ እና በግል ጥቅም ተደልሎ የሃሰት ምስክር እንደማይሰጥ ለፋሺስት አብይ አህመድ እና የብልፅግናው ቡድኑ በተደጋጋሚ መልስ ቢሰጠውም አሁንም በጃል በቴ ኡርጌሳ ወንድምና ቤተሰብ ላይ ተመሳሳይ ጫና ማድረጉን ቀጥሎበታል።
አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ሰኔ 28፣ 2024 ባገኘው መረጃ ምንም እንኳን በሰኔ 8፣2024 ዘገባው ላይ (ወደ ታች ወረድ ብለው ያንብቡ) አሻፈረን አንዋሽም ታሪካችንን ማበላሸት አንፈልግም ቢሉም የእውሸት ቋቱ ፋሺስት አብይ በቡድኖቹ አማላጅነት አሀንም ለእኛ መስክሩልን እያለ እያሰቃያቸው ይገኛል።
የሃሰት ምስክር እንዲሰጡ የተጠየቁት፣ መልስና የዕቀባ ዉሳኔ
ሰኔ 8፣ 2024 ማንነቱ እንዳይጠቀስ ከፈለገው እና በዱግዳ ወረዳ፣ መቂ ከተማ ውስጥ የሚኖረው የከተማው ፖሊስ ከፋሺስት አብይ ተላላኪና ገዳይ ቡድን ለጃል በቴ ኡርጌሳ ወንድሞች ቄሮ ሚሎ ኡርጌሳ እና ሹቡላ ዋኔት የተስጣቸው የሃሰት መስካሪነት ጥያቄ እና መልሳቸውን እንዲሁም የፋሺስቱ ብልፅግና ገዳይ ቡድን የዕቀባ ውሳኔ እንደሚከተለው አብራርቶ ለአቢኦ አሳውቆዋል፦
“የገደልነው እኛ ነን በሉና መስክሩ፣ በሚድያችን (OBN) እናቀርባችኋለን፣ ከመሰከራችሁም በኋላ ሐገር ውስጥ መኖር ካልፈለጋችሁ ገንዘብም ሆነ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አስተካክለን ወደ ውጪ ሐገር እንልካችኋለን። እኛ ወደምናዘጋጅላችሁ ሐገር መሄድ ካልፈለጋችሁ ፓስፖርታችሁን እናዘጋጅላችኋለን፣ ገንዘብም እንሰጣችኋለን፣ ጉዞዋችሁንም በቦሌ በኩል እናመቻችላችኋለን።”
“ወንድማችን ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እታገላለሁ ብሎ በገባው ቃል መሰረት የማይተካውን ህይወቱን እንደ ዓይን ብሌኑ ለሚያየው ህዝቡ የሰጠ ነው። በህይወቱ ዘመንም ተፅእኖ የሚፈጥሩ ለኦሮሞ ህዝብ ይመጥናሉ ብሎ የሚያስባቸውን ሃሳቦች ይዞ በመድረክ ላይ ይታገል የነበረና ሃሳቡንም ማሸነፍ ያቃታቸው የሞራልም ሆነ የሃሳብ ልዕልና በሌላቸው እጅ ህይወቱን ተነጥቀናል። የጀግናውን የጃል በቴ ኡርጌሳን ታሪክ የሚያጎድፍ የእውሸት ምስክር አንሰጥም። እኛ አልገደልነውም። ያደረግነውን እንጂ ያላደረግነውን አድርገናል ብለን አንመሰክርም። ለግል ጥቅማችን ብለን የራሳችንንም ታሪክ አናጎድፍም። ከፈለጋችሁ እኛንም እርሱን በገደላችሁበት ጥይት ግደሉን!”
ከዚህ በላይ ያለውንም መልስ ታስረው ከሚሰቃዩት የጀግናው ጃል በቴ ኡርጌሳ ወንድሞች ለፋሺስት አብይ ተላላኪዎች እና የገዳይ ቡድኑ መልሳቸውን እንደሰጡም፣ ሃሳባቸው ተቀባይነት ማጣቱን በመገንዘብ የክስ መዝገባቸው በዱግዳ ወረዳ፣ በመቂ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ፍርድ ቤት እንዳይታይ ዕቀባ አድርገውባቸዋል።
“ጅብ በቀን ያደረገውን ያውቃል ስለዚህም በሌሊት ይሸሻል” እንደሚባለው ይህም ዳግም የፋሺስት ብልፅግና ገፅታ መሆንን ከጀመረ ውሎ አድሮዋል። ይኸውም በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሺን (ለሙሉ ሪፖርቱን ይህንን ገፅ ይጫኑ https://addisstandard.com/bate-urgessa-olf-political-officer-shot-dead-in-meki-town-oromia-region/) ስለ ጃል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ለማወቅ ሶስት ሰዎችን ወደ ተገደለበት ቦታ ልኮ ምርመራ ቢጀምርም በዚያን ዕለት በቦታው ከተገኙት ሰዎች መረጃ ወስዶ ሳይጨርስ የማፍያው ፋሺስት አብይ ብልፅግና ቡድን እነዚያን ሰዎች አሰረ። ከጃል በቴ ወንድሞችም መረጃ እንዳይወስድ እነሱንም ወደ እስር ቢት ከተታቸው። በመጨረሻም ኮሚሽኑ ምርመራ እንዳያካሂድ እና እውነታውን ለመቅበር መከልከሉ ይታወሳል።
በቦረና ዞን የተፈጥሮ እና የሰው ሰራሽ ተፅእኖ በህዝቡ ላይ የበረታ መሆኑ የታወቀ ነው። ስለሆነም መምህራኖች ደግሞ ይህን ሁሉ ችግር በመቋቋም ትውልድን እየቀረፁ ያሉ ቢሆንም የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን በእነርሱ ላይ ከባድ ተፅእኖዎች እያደረገ ይገኛል። ይህንኑ ስልት ለማጠናከር ሚያዚያ 16፣ 2024 ቢቂላ ታደሱ የተባለ መምህርን የጃል በቴ ኡርጌሳ ፎቶ በሞባይል ስልኩ ውስጥ በመገኘቱ ምክንያት ብቻ “ይሄ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ደጋፊ ነው” በማለት ያለ አንዳች ጥፋት ይዘው በወረዳው የፖሊስ ጣቢያ አስረው እያሰቃዩት እንደሆነ የቀበሌው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልፀዋል።
ኢምፓየሪትዋን ከመሰረትዋ ፈንቅሎ ለመጣል በ11ኛው ሰዓት ላይ የሚገኘው ትውልድ በገንዘብ ተደልሎ የሃሰት ምስክር እንደማይሰጥ ለፋሺስት አብይ አህመድ እና ለቡድኑ በተደጋጋሚ ተገልፆላቸዋል። እርማችሁን አውጡም እንላለን።
#የሽኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
