• Wed. Nov 25th, 2026

በሰሜን ኦሮሚያ በወሎ ዞን የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን በመሃከላቸው የተፈጠረውን ክፍፍል ለመሸፈን ያደረገው ጥረት በአባ ገዳዎችና በሐገር ሽማግሌዎች ከሸፈ

Jul 7, 2024

ሐምሌ 6፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በፋሺስቱ ብልፅግና መዋቅር መካከል የተፈጠረውን መከፋፈል ለመሸፋፈን የፋሺስት አብይ አህመድ ካድሬዎች አባ ገዳዎችን እና የሐገር ሽማግሌዎችን ወደ ስብሰባቸው ጠርተው የእውሸት ፕሮፖጋንዳ ለማቀናጀት በከሚሴ ከተማ እያካሄዱ እንደነበረ አቢኦ ከምንጮቹ ደርሶታል።

በከሚሴ ከተማ ውስጥ በመዋቅር መካከል ያለው ጥል ከአንድ ወር በላይ የቆየ ሲሆን አቢኦ ዘግቦ እንደነበረ እና እርስ በእርሳቸው መገዳደላቸውም የሚታወስ ነው። በይፋ ሲሰሩ ከነበረው ወንጀል እራሳቸውን ነፃ ለማድረግ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ስም ለማጠልሸት እየሞከሩም ይገኛሉ።

የዞኑ አስተዳዳሪ በፓርቲያቸው መካከል ያለውን ቅራኔ ለመደባበስ በመዋቅራቸው ውስጥ ከታች ያሉትን አካላት፣ የፌደራል አካላትን እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች እና አባ ገዳዎችን ያካተተ ስብሰባ ሰኔ 8-11፣ 2024 አድርገው ነበር። በዚሁ ስብሰባ ላይ ለሃገር ሽማግሌዎች እና አባ ገዳዎች የሚከተለውን ብለዋል፥ “እኛ አንድነት የለንም። ከህዝባችን ጋር አንድነትን ማጠናከር እንፈልጋለን፣ የእኛ መንግስት ህዝብ ነው። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መሳሪያ ፈትቶ እንዲገባ እዘዙት። እምቢ ካለ ጠንካራ አቅም አለን እናም እንደመስሳቸዋለን!” ሆኖም ግን ይህ ዛቻ በአባ ገዳዎቹ እና የሀገር ሽማግሌዎቹ ተቀባይነት አላገኘም።  

አባ ገዳዎቹ እና የሀገር ሽማግሌዎቹም በጥሞና ካዳመጥዋቸው በኋላ የሚከተለውን ምላሽ እንደሰጡ አቢኦ ከምንጮቹ አግኝቶዋል። “እናንተ የምትሉት ህዝብ የትኛው ነው? ያለ አንዳች ወንጀል በገዛ ቀዬው እየዘረፋችሁ፣ እያሰራችሁ እና እየገደላችሁ የቆያችሁት አይደለምን? ኦሮሞ በቅኝ ገዢዎች እጅ ከወደቀበት ግዜ ጀምሮ በነበሩት የስርዓቱ መሪዎች ያልተደረገ ግፍ እና እንዲህ ብዛት ያለው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ተፈፅሞብን አያውቅም። በአሃዝ ሲነፃፀርም በብልፅግና መንግስት ዘመን የተጎዳነው ጉዳት ካለፉት 100 ዓመታት ይበልጣል።” ይህም ምላሽ የብልፅግናውን ከፍተኛ አመራሮችን እና የዞኑ ካቢኔዎችንም ጭምር የበለጠ እንዲወዛገቡ አድርጎዋል።

ከአባ ገዳዎቹና ከሐገር ሽማግሌዎቹ ከተሰነዘረባቸው ትችት በላይ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ፋኖንም ጨምሮ ዞኑን ጥሰው በመግባት ህዝቡን ሲወጉ በቆዩበት ግዜ ህዝቡ እርዳታ ቢጠይቅም አጥጋቢ መልስ እና እርዳታ ከመንግስት አለማግኘቱ በዚህ ወንጀል ውስጥ መንግስትም እጁ እንዳለበት ያሳያል።

የብልፅግና መንግስት አካል ከማህበረሰቡ ማለትም ከአባ ገዳዎቹና ከሐገር ሽማግሌዎቹ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ መመለስ ባለመቻላቸው ስብሰባቸውም ያለምንም ውጤትና ውሳኔ ሰኔ 11፣ 2024 መበተኑን ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ከስብሰባው ተካፋዮች መረጃ ደርሶታል።

#የሽኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

Leave a Reply