• Tue. Nov 24th, 2026

በሽኒጋ ቃል-ኪዳን ስምሪት የምስራቅ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምዕራብ ሐረርጌ በሀብሮ ወረዳ ውስጥ ጠላትን በሙት እና በቁስለኛ ቀጣ

Jul 7, 2024

ሐምሌ 2፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻውን በማጠናከር  በፋሺስት የብልፅግና ጦር ላይ የማያዳግም እርምጃዎችን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።

በዚሁ ሁኔታ ልበ ብረቶቹ የምስራቅ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ በሃብሮ ወረዳ፣ በዱግዳሚ አፉር ቀበሌ ዲክቻ በተባለ ቦታ ሰኔ 13፣ 2024 የማፍያው አብይ አህመድ ጦር በአሰሳ ስም የኦሮሞ ህዝብ ላይ ይቅር የማይባለውን ግፍ ሊከውኑ የወጡትን አድፍጦ በማጥቃት አራቱን ወዲያውኑ ሲገድል፣ ስድስቱን ደግሞ ክፉኛ አቁስሎ የተረፉትም በተለያየ አቅጣጫ ወደ መጡበት ተመልሰዋል።

በዚህ እርምጃም ሁለት AKM እና ሁለት ፋል ጠመንጃዎችን ከጠላት ጀርባ በመፍታት ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ገቢ አድርጓል።

#የሽኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብ እና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply