• Wed. Nov 25th, 2026

አምባገነኑ የብልጽግና ቡድን በኢሉ አባ ቦራ ዞን ዝርፊያ በሰፊው ሲያካሂዱ በጂማ ከተማ ደግሞ የህዝብ ቤቶችን እና ንግድ ቤቶችን በማፍረስ በርካታ ሰዎችን የጎዳና ነዋሪ አድርጎዋቸዋል

Jul 7, 2024

ሐምሌ 2፣ 2024 አራት ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ኢሉ አባ ቦራ ዞን

ሰኔ 14፣ 2024 በአሌ ወረዳ፣ የጎሬ ከተማ አስተዳደር የሰላም ጉዳይ ቢሮ እና የከተማው ፖሊስ በከተማው ውስጥ የሚገኙትን የምግብ ቤት ባለቤቶችን እና ነጋዴዎች ጋ እየሄዱ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ላይ 500-1000 ብር እንዲሁም ገቢያቸው ከፍተኛ ከሚባሉት ደግሞ ከ5000-10,000 ብር ለሞተር ሳይክል መግዣ ያስፈልገናል በሚል ሰበብ የመሳሪያ አፈሙዝ በፊታቸው በመደገን እና በማሥፈራራት ለሶስት ቀናት ሲዘርፉ እንደነበረ የአካባቢው ህዝብ ለአቢኦ ተናግረዋል።

ይህም ድርጊት ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ተጨምሮ ህዝቡን ጭንቀት ውስጥ መክተቱን ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ጨምረው ተናግረዋል።

ጂማ ከተማ 

የብልፅግና ማፍያ ቡድን የዘረኝነት ፖለቲካን በመፀንሰስ የሚታወቅ ሲሆ ከቅርብ ግዜ ጀምሮ የድሀ እናቶችን ቤት ጠጋኝ በመምሰል በብዙ የኦሮሚያ ከተሞች የህዝብ ቤቶችን እና የንግድ ቤቶችን እያፈረሰ ይገኛል። ይህንንም እኩይ ድርጊት ሰኔ 1፣ 2024 በጂማ ከተማ፣ ጊንጆ እና አጂፒ ቀበሌዎች ውስጥ ቡና ቤቶች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ሆቴል እና ትላልቅ ሱቆችን ጨምሮ ከ50 በላይ ማፍረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል። የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑት ግለሰቦች ለፈረሰባቸው መኖሪያ ቤትም ሆነ የንግድ ቤት ተተኪ ቦታም ይሁን ካሳ እንዳልተሰጣቸው ነዋሪዎቹም ጨምረው ገልፀዋል። 

ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች አብዛኞቹ አነስተኛ ገቢ ያላቸው በመሆኑ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ያለምንም መጠለያ መንገድ ላይ ዝናብና የፀሀይ ሃሩር እየተፈራረቀባቸውም ሲገኙ፣ ይህም ለበሽታ እያጋለጣቸው መሆኑን የእቢኦ ምንጮችም ተናግረዋል::

የኢትዮጵያ ኢምፓየር ጠባቂዎች የኦሮሞን ህዝብ በማሰር፣ በመዝረፍ፣ ቤቱን በማፍረስ እና ቤትና ንብረቱንም በእሳት በማጋየት ከቀዬው ማፈናቀልንም ስራዬ ብለው አጠናክረው ቢቀጥሉም፣ የኦሮሞን ህዝብ ቁርጠኛ የነፃነት ትግል ያነገበውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ግን ወደፊት ከመገስገስ ሊገድቡት አልተቻላቸውም።

#የሽኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

Leave a Reply