ሐምሌ 2፣ 2024 አራት ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የቅኝ ገዢው የብልፅግና ቡድን በህዝቦች መካከል አደገኛ እና የተጠላለፈ ሴራ ማሴሩን ቀጥሏል። ይህንኑ የጎንዮሽ ጥቃት መሰረት በማድረግ የግሙዝ እና የኦሮሞ ህዝብን በማጋጨት የግሙዝ ተወላጆች ኦሮሞዎችን በቀስት እና እነርሱንም በማስታጠቅ በጥይት እንዲገድሉዋቸው እና የተረፉትን ደግሞ እንዲፈናቀሉ እያደረገ ይገኛል።
ለሶስት ቀናት ማለትም ግንቦት 22 – 24፣ 2024 በመተከል ዞን፣ በድባጤ ወረዳ በሶስት ቀበሌዎች ውስጥ የግሙዝ ታጣቂዎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ ተኩስ በመክፈት ብዙ ሰዎችም እንድተጎዱ የአቢኦ ምንጮች ተናግረዋል። አያይዘውም ይህንኑ ጦርነት እንዲፈፀም ካደረጉት ሰዎች መሃከል የሀሮ ሊሙ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደቻሳ ሃይሌ እንዳለበትም ገልፀዋል።
በዚህ ጦርነት በሀሮ ሊሙ ወረዳ ከሶስት ቀበሌዎች፣ ማለትም ከሱካን፣ አሙሩ እና ዳሌ ቀበሌዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ቀዬአቸውን እና ንብረታቸው ትተው ተፈናቅለዋል። በተጨማሪም ለዚህ ይቅር ለማይባል የዘር ማጥፋት ወንጀል ጠንሳሹም የሀሩ ሊሙ አስትዳዳሪ (አቶ ደቻሳ ሃይሌ) መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል። ይኸውም ፀቡ ከመቀስቀሱ በፊት አስተዳዳሪው ወደ ያሶ በመደወል “በመካከላችን ጠላት አለና ጠላትን ከመካከላችን አውጣ!” ማለቱንም አክለው ገልፀዋል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት፣ እና ንጹሃን ኦሮሞን በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ካድሬዎቹን ለማዘዝ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
