• Tue. Nov 24th, 2026

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምስራቅ ወለጋ በሳሲጋ ወረዳ በጠላት ተላላኪ ጦር ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

Jul 20, 2024

ሐምሌ 19፣ አራታ በዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) 

የኦሮሞ ህዝብ ክንድ እና ጋሻ የሆነው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምስራቅ ወለጋ በሳሲጋ ወረዳ ውስጥ የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻን ተመርኩዞ ከሐምሌ 8 እስከ ሐምሌ 9፣ 2024 በወሰደው የማያዳግም የማጥቃት እርምጃ የጠላት ሴሎችን በሙት እና በቁስለኛ መቅጣቱን ለአቢኦ በቃል አቀባዩ በኩል አሳውቆዋል።

ሐምሌ 8፣ 2024 አባ ዳሌ በሚባል ቦታ ላይ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን እናስሳለን በሚል ሰበብ በተሰማራው የጠላት ተላላኪዎች ላይ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ በርካቶችን ሲገድል፣ የተቀሩትን ደግሞ ማገገም በማይቻል ቁስለኛ መቅጣቱ ታወቀ።

ሐምሌ 9፣ 2024 በኦዳ ቀበሌ ቦሶቃ በተባለ ቦታ ላይ እንዲሁ የኦሮሞን ህዝብ ለማሰቃየት የተሰማሩት የፋሺስቱ አብይ አህመድ ወታደሮች አድፍጦ በመጠበቅ እየመጡ ባሉበት ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት በመክፈት ከስረዓቱ ጦር ብዙዎቹን በመግደል ሌሎቹንም ማገገም በማይቻል ቁስለኛ በመቅጣት ሸንቷል። በዚህም የጥቃት እርምጃ አንድ ኤኬኤም ጠመንጃ እና ሙሉ የወገብ ትጥቅ በመፍታት ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ካምፕ ገቢ አድርጓል።

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply