ሐምሌ 24፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በስመ ሰላም እንጠብቃለን ሰበብ በገጠሩ ኦሮሚያ እየተሰማሩ ያሉት የቅኝ ገዢው የብልፅግና ጦር ሀብት መዘረፍ፣ ቤት ማቃጠል፣ ሰዎችን በጅምላ ማሰር እና ግድያ መፈፀሙን አጠናክረው ቀጥለዋል።
በኦሮሚያ የህግ የበላይነትን እናስከብራለን በሚል ስም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በበልፅግና ቡድን ከታወጀ አመታትን አስቆጥሮዋል። ይህም አዋጅ ለፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን ጾታ ሳይለይ አዛውንትን፣ ቄሮና ቃሬ፣ በተለያየ የግል ማለትም በንግድና በእርሻ ስራዎች ተሰማርተው እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተደራድሩ ኦሮሞዎች ላይ ላደረሰውና እያደረሰ ላለው የጦር ወንጀል እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ አመቺ መስፈርት ዘርግቶለታል። ይህንንም ግብ ለማድረስ በተለያየ ግዜ የተለያዩ የግፍ ስልቶችን እየቀረፀም የኦሮሞን ህዝብ የመኖር ህልውና እየገፈፈም ይገኛል።
ይህንንም የግፍ ስልት የፋሺስት ብልፅግና ቡድን ጦር በምዕራብ ሸገር ዞን፣ በሜታ ወልቂጤ ወረዳ ለረጅም ግዜ በተግባር ሲያከናውን ቆይቶዋል። ሐምሌ 7፣ 2024 ደግሞ በሜጢ ሀሮ ቀበሌ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን እናስሳለን በሚል ሰበብ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የጦር ቡድኑ ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩት፦
- ኦቦ ቶሎሳ ሞኮንን፣
- ኦቦ በdhaadhaa ጋረማ፣
- ኦቦ ደምሶ ጋረማ፣
- ኦቦ ቶሎሳ ያደሳ፣
- ኦቦ ሽፈራ አመንሲሳ፣
- ኦቦ ታዬ ኮርሳ፣
- ኦቦ ደረጄ ለገሳ እና
- ኦቦ ቀነኒ በdhaaሳ ይዘው፣ እስር ቤት ውስጥ አጉረው እያሰቃዩዋቸው መሆናቸውን አቢኦ ከምንጮቹ አግኝቷል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
