• Wed. Nov 25th, 2026

የመካከለኛው ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምዕራብ ሸገር ዞን፣ በሚዳቀኚ ወረዳ ከ50 በላይ የጠላትን ጦር ወደ ማይመለሱብት ሲሸኝ ብዙዎችንም ማርኳል

Jul 24, 2024

ሐምሌ 24፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ጀግናው የመካከለኛው ዞን የአሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምዕራብ ሸገር፣ በሚዳቀኚ ወረዳ፣ ገራዶ በተባለ ቦታ ሐምሌ 15፣ 2024 ጠላትን እርም በሚያስብል ሁኔታ እርግፍ ከማለትም በላይ በሙት እና በቁስለኛ በመቅጣት ሌሎቹን ማርኳል።

በዚህ እርምጃ አንበሶቹ የመካከለኛው ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት 52 የፋሽስቱን የብልፅግና ጦር ከደቼ ከመቀላቀሉም በላይ 13ቱን ማርኳል። በርካታ የጦር መሳሪያዎችንም ከጠላት ወገብ ላይ በመፍታት ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ገቢ አድርጓል።

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply