ነሐሴ 18፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ምዕራብ ሸገር ዞን፣ ጀልዱና ጮቢ ወረዳዎች
የፋሺስት ብልፅግና ጦር ቡድን “ከ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አላችሁ።” በሚል የሃሰት ወንጀል ከኦሮሞ አርሶ አደሮች የተለያዩ አዝርእቶችን እንደ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ እና ጤፍ የመሳሰሉትን በአጠቃላይ በጎተራቸው እና እቤታቸው ውስጥ ያገኙትን ሁሉ መዝረፋቸውን አጧጡፈው ቀጥለዋል። የዘረፏቸውንም ግለሰቦች ከባድ ድብደባ ከፈፀሙባቸው በኋላ ወደ እስር ቤት ማጋዛቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ጨምረው ተናግረዋል።
ከዚህ ሌላ ገበሬው ማሳውን እንዳያርስ በመደረጉ ይህንንም ውሳኔ የጣሰ እንዲገደል በፋሽስት ብልፅግና ቡድን አዛዦች ተወስኖዋልም ተባለ። ኦቦ ቶሎሳ በሪ የሚባሉ ግለሰብ ይህንን የወንጀል ውሳኔ በመቃወማቸው በጥይት ተመትተው መቁሰላቸውን የአቢኦ ምንጮች ተናገሩ። በተፃራሪው ስርዓቱ የሾማቸው ሚሊሻዎች
የአርሶ አደሮችን መሬት በመውሰድ ለራሳቸው እያረሱ እንደሆነም አክለው ገልፀዋል።
በምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ጉቶ ጊዳ ወረዳ
የፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና ስርዓት ለማቆየት የጦር ቡድኑ እና ካድሬዎቹ በመመሳጠር ከሆሮ ሃለቱ ከተማ በርካታ ሰላማዊ ህዝብን ያለ አንዳች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሰር፣ መዝረፍ እና መግደላቸውንም ቀጥለዋል።
በግንቦት 20፣ 2024 ከሆሮ ሃለቱ ከተማ ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘረው፦
- ኢዶሳ ፈይሳ
- ቡሳ ወርቂ
- ሀሩን አብዱ
- ለሜሳ ወርቁ እና
- ፈይኔ ገመቹ መታስራሳቸውን አቢኦ ገልፆ ነበር። አሁንም በፋሺስቱ እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።
ከዚህ ሌላም ሐምሌ 20፣ 2024 የፋሺስቱ ብልፅግና መዋቅር “የፓርቲ ድጋፍ” በሚል የሟሟከሻ ስም ህብረተሰቡን በግድ ሰብስበው፣ በስብሰባውም ላይ ተቃውሞዋቸውን ያሰሙትን ሰዎችም ወደ እስር ቤት እየተጋዙ መሆናቸውን የጉቶ ጊዳ ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገሩ። የከተማው ከንቲባ አቶ መልካሙ ገዲሳ አክለውም እውነት በመናገራቸው ብቻ መብታቸውን የጠየቁ እና ሃሳባቸውን የገለፁትን ተሳታፊዎች ለማሰር እና ለማስፈራራት በአሁኑ ወቅት ሚሊሻዎች ተሰማርተው ይገኛሉም ብለዋል።
ከሚዘርፉት ገንዘብ ውስጥም 12% ለፓርቲያቸው እንደሚግባና የቀረውን ሰብሳቢዎቹ ወደ ግል ኪሳቸው እንደሚያስገቡት የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግሮዋል። ይህም የሚያሳየው የፋሺስቱ ብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ደመወዝ መክፈል ስለማይችል በዚሁ ዘረፋ የሚያካክስላቸው ይመስላል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ፣ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
#ጨቋኙ_ኃይል_በኦነሰ_ኃይል_ይገረሰሳል!
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
