• Thu. Mar 19th, 2026

የጭቁኑ ኦሮሞ ሕዝብ ነፃ አውጪ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ማዕከላዊ ዞን፣ በምስራቅ ሸገር ሃርሰዲ እና ምዕራብ ሸገር በጠላት ላይ ከባድ እርምጃ መውሰዱን አሳወቀ

Aug 18, 2024

ነሐሴ 18፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

እራሱን እንደ ሻማ እያቀለጠ የነፃነት ብርሃን ጮራን በማስፈነጠቅ ላይ ያለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት፣ በጽኑ አላማ መነሳቱን ለማሳየትም ከዕለት ዕለት አመርቂ ድሎችን እያስመዘገበ ይገኛል።

የኦነስ ማዕከላዊ ዞን፣ ምስራቅ ሸገር ሃርሰዲ

የኦነሰ ነሐሴ 9፣ 2024 ፈንታሌ ወረዳ ጊዲራ ወበሌ በተባለ ቦታ በወሰደው የማጥቃት እርምጃ አራት የፋሺስት ብልፅግና ስርዓት ዘብ ጠባቂዎችን እረፍት ሲሰጥ ዘጥኙን ደግም በማይሽር ቁስል ሸኝቷል። 

በዚህም ውጊያ የሚከተሉትን የጦር መሳሪያዎች ከጠላት ጀርባ በመፍታት፦

  • አንድ AKM፣
  • አንድ SKS፣ 
  • 46 የእስናይፐር ጥይቶች እና
  • ሙሉ ትጥቅ እንዲሁም ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ገቢ አድርጓል።

በዚህ ውጊያ የተደናገጡት የስርዓቱ ዘብ ጠባቂዎች የአከባቢውን ህዝብ ሲያሸብሩ እንደነበረም ነዋሪዎቹ ለአቢኦ ተናግረዋል።

የኦነስ ማዕከላዊ ዞን፣ ምዕራብ ሸገር

የህዝብ አለኝታው የኦነሰ በጀልዱ ወረዳ፣ ኪልቤ ቀበሌ ጠላት ሰፍሮበት በነበረው ቦታ ላይ ነሐሴ 8፣,2024 አድፍጦ በወሰደው እርምጃ 14ቱን ከአፈር ሲቀላቅል 17ቱን ደግሞ ክፉኛ አቁስል ሸኝቷል።

በዚህም ውጊያ ጠላት ከባድ ፍራቻ ውስጥ ከመግባቱም የተነሳ ተጨማሪ ኃይል ሲጠራ እንደነበረም ታውቋል።

#ጨቋኙ_ኃይል_በኦነሰ_ኃይል_ይገረሰሳል!

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading