• Sat. Mar 14th, 2026

በፋሺስት አብይ አህመድ የሚደገፋት ጽንፈኞቹ የአማራ ፋኖ ኃይሎችና የፋሽስት ብልፅግና ሰራዊት በሰሜን ሸገር ወረዳዎች ደራ ወረዳንም ጨምሮ የኦሮሞን ህዝብ አፍኖ መሰወር፣ ማሰቃየት እና መግደል ቀጥለዋል

Oct 15, 2024

ጥቅምት 12፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የጽንፈኛው አማራ ፋኖ ቡድን በኦሮሞ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ለማካሄድ በብልፅግናው መንግስት በመደገፍ ከባድ ጉዳት በኦሮሞው ህብረተሰብ ላይ እያደረሱ መሆናቸውን ተገልጿል።

ፅንፈኛው የአማራ ፋኖ ኃይሎች ጥቅምት 5፣ 2024 ምሽት ላይ በደራ ወረዳ፣ መካፍታ ቀበሌ፣ ልዩ ስሙ ሀርቡ መስቀሌ በተባለ ቦታ ላይ ተሰማርተው አዴ አሰገዱ ፀጋ የተባለችውን እናት እቤትዋ ድረስ በመሄድ ከያዝዋት በኋላ ጥይት እንደ ዝናብ በማዝነብ አረመኔያዊ ግድያን ፈፅመውባታል።

እንዲሁም ጥቅምት 8፣ 2024 የኢምፓየሪቱ መከላከያ ሰራዊት አባል እና ከአማራ ብሄር የሆነ በደራ ወረዳ፣ ኦርጎ ቀበሌ ውስጥ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ተኩስ በመክፈት ጉዳት ካደረሰ በኋላ ወደ ጽንፈኛው የአማራ ፋኖ መቀላቀሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።

በሰሜን ሸገር ዞን፣ ደራ ወረዳን ጨምሮ በበርካታ የዞኑ ወረዳዎች ውስጥ ኔትወርክ ከተቋረጠ በኋላ የፋሺስት ብልፅግና ሰራዊት እና በፋሺስት አብይ የሚደገፈው ጽንፈኛው የአማራ ፋኖ የሰብዓዊ መብት ረገጣውን አጠናክረው መቀጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።

በተለይ እንደ ደራ፣ ወረ ጃርሶ፣ ቀሬ ጎሀ፣ አቦቴ ኤጄሬ፣ ኩዩ-ገርባ ጉራቻ፣ ደገም ሀምቢሶ፣ ሱሉልታ ጫንጮ፣ ግራር ጃርሶ-ፊቼ፣ ውጫሌ-ሙካ ጡሪ፣ ያያ ጉለሌ እና ሰንዳፋን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ረገጣው በከፋ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ እስከ ነፃነት በሚል መርሆ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading