የኦሮሞን ጠላቶች አደራጅቶ: አስታጥቆ: ያሰማራው: የሚያሰማራው ብልጥግና ነው::
ትናንትናም ዛሬም: ኦሮሞን የሚገድለው: የሚያርደው: የሚያሳርደው ኦ-ብልጥግና ነው::
ፋኖንም ሆነ ሌሎች አማርኛ ተናጋሪ አደረጃጀቶችን አሰልጥኖና አስታጥቆ በኦሮሚያ ውስጥ ያሰማራው: ኦሮሞን ያፈናቀለው: የኦሮሞ ንብረቶችን የዘረፈው/ያስዘረፈው: ያቃጠለው/ያወደመው ብልጥግና ነው::
በወሎም: በደራም: በከረዩም: በጉጂም: በወለጋም: በፊንፊኔም ኦሮሞን ያስፈጀውና የፈጀው ብልጥግናነው::
በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሁለንተናዊ የዘር ማጥፋት ለመፈፀም እቅድ አውጥቶ: ፖሊሲ ነድፎ: አሰቃቂ ወንጀሎችን የፈፀመው: ያስፈፀመው: የነ ፍቃዱ ጡዌ ብልጥግና ነው::
ኦሮሚያን ለማፍረስ: በታትኖ 5 ክልል ለማድረግ እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ የነበረውና ያለው: የአብይ አህመድና የሽመልስ አብዲሳ ብልጥግና ነው::
ድንበሩን ለማናጋት: በሶማሊ: በከረዩ: በጌዲኦ: በጉሙዝ: በጋምቤላ: በአማራ: በአፋር በኩል ያሉ ታጣቂዎችን ቀስቅሶ ለብዙዎች እልቂትና መፈናቀል ምክንያት የሆነው: ብልጥግና ነው::
ባጠቃላይ: ኦሮሚያን ያናጋው: ሕዝቡንም ሁለንተናዊ ደህነት ያሳጣው: ብልጥግና ነው::
የኦሮሞ መሪዎችን አስሮ: ለዓመታት ያለ ክስና ፍርድ ሲያንገላታ የነበረው ብልጥግና ነው::
የጸጥታ/የሰላም ኮሚቴ” (ወይም “Korree Nageenya”) ተብሎ በተሰየመው የግድያና የኣፈና ቡድን በመጠቀም: የኦሮሞን ሕዝብ ያለ መሪና ያለ ተስፋ ለማስቀረት: እንደ በቴ ኡርጌሳ ዓይነቶቹን መሪዎች ያረደው: አንዳንዶቹንም ገድሎ አስከሬናቸውን ለጅብ የሰጠው ኣራጅ ቡድን: ብልጥግና ነው::
እንደ ሃጫሉ ሁንዴሳ ያሉ: አርኣያ የሆኑ የኪነ-ጥበብ መሪዎችን: ያረደው: እና በሞቱም የተሳለቀው: በባህሉና በማንነቱ የሚኮራ: በእራሱ የሚተማመን ትውልድ በኦሮሞ ውስጥ እንዳይፈጠር: ተግቶ የሠራውና አሁንም እየሠራ ያለው ብልጥግና ነው::
የኦሮሞን መሬት: ሃብትና ንብረት: ለሌሎች አሳልፎ የሰጠው: የሸጠው: አልፎም ለስልጣን ማስጠበቂያ: ወዶ-ገቦችን ለመደለያ: ደጋፊ ግለሰቦችን አደልቦ “ባለጊዜ” ለማሰኘት እየሠራ ያለው የዘራፊና የአስዘራፊ ስብስብ ብልጥግና ነው::
የኦሮሞ ሕዝብ የሚታገለው: የእኩልነትና የነፃነት መብቱን: የአገር ባለቤትነቱን የነጠቀውን ግፈኛ ሥርዓት
ነው::
የዚህ ሥርዓት የወቅቱ ባለቤትና ጠባቂ: የመንግሥትን ሥልጣን ተቆጣጥሮ: የግፈኛው ሥርዓት አስተግባሪና ተጠቃሚ ሆኖ ያለው: “ብልጥግና” ብሎ እራሱን የሚጠራው የዘራፊና የዘር-ኣጥፊዎች ቡድን ነው::
ደግመን ደጋግመን አንድ ነገር ግልፅ እናድርግ:- የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሚዋጋው: በዋናነት: ከሥርዓቱ ጋር ነው::
እንደ ነፃነት ሠራዊት: ኣትኩሮቱ: ነፃነቱን ከነፈገው ሥርዓትና መንግሥት: እንዲሁም መንግሥት ካሰማራቸው የቅርብና የሩቅ ጠላቶች ጋር ነው::
ሌሎች ኃይሎች የኦሮሞን ሕዝብም ሆነ ሌሎች የአገሪቱን ሕዝቦች ሲያጠቁ የመከላከል ሃላፊነት: የመንግሥት ነው::
ወንጀልን መቆጣጠር: ሕግን ማስከበር: የህዝቡን ሰላምና ፀጥታ የማስጠበቅ ግዴታ የመንግሥት ነው::
መንግሥት ተብዬው ይሄን ማድረግ ካቃተው: ለሚደርሰው ጥፋት ተጠያቂ የሚሆነው: እራሱ (መንግሥት) ነው:: ሕዝቡ: ለመንግሥት ግብር የሚከፍለው: በቀዳሚነት ይሄንን ሥራ እንዲሠራለት ነው:: ይሄን ማድረግ ካቃተው: ግብር የከፈለው ሕዝብ ሆ! ብሎ ተነስቶ ማባረር ያለበት መንግሥት ነኝ ባዩን ቡድን ነው::
መንግሥት ሥራውን መስራት ሲያቅተው: “መንግሥትን ተክቶ ህዝብን የማስተዳደር ሥራ: የነፃነት ሠራዊቱ ነው” የሚል ሕገ-መንግሥት ወይም የፖለቲካ ፅንሰ-ሃሳብ በምድር ላይ ተሰምቶም አይታወቅም: የለምም:: እንዲህ ያለው ኣስተሳሰብ: የደናቁርት አስተሳሰብ ነው:: ይሄ ያላዋቂ ሰው: የተደናበረ ሰው: ወይም የእነ ሽመልስ ኣብዲሳ ደንባራ አስተሳሰብ ነው:: ይሄ: አውቀው የደነቆሩና የተደናበሩ ኣደናባሪ ካድሬዎችና (የመንጎቻቸው) አስተሳሰብ ነው::
የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት: የመንግሥትን ገዳይ ሠራዊት ለመዋጋት እንጂ እሱን ለመጠበቅና ለመንከባከብ ከቤት አልወጣም:: ዓላማውም በየትኛውም ቦታ: ጊዜና ሁኔታ: የመንግሥትን ኃይል መውጋት: ማዳከም: ማንኮታኮትና ማፍረስ ነው:: “ለምን ይወጋናል?” ለሚለው ለሽመልስ አብዲሳ የጅል ለቅሶ: መልሳችን: “ገጥመን መስሎን!” የሚል ይሆናል:: ኣዎን: ዛሬም: ወደፊትም WBO ይወጋቸዋል:: ይሄን ካደረገ ደግሞ ሥራውን በአግባቡ ሠርቶአል ማለት ነው::
ይሄን እያደረገም: በእነሱ ልዩ ኃይል: መከላከያና ሚሊሻ ታግዞ ህዝቡን ሊፈጅ የተሰማራውን ማንኛውንም ኃይል በየደረሰበት ሲታገልና ህዝቡን ከነዚህ ኃይሎች ሲታደግ የነበረ መሆኑን: በወለጋም: በከረዩም: በደራም: በሰላሌም በተለያዩ ጊዜኣት አሳይቶኣል:: ይሄንንና እንዲህ ያለውን የመንግሥት ቅጥረኛ ሁል ጊዜም ይፋለማል:: ዋና ዒላማውም: ትኩረቱም መንግሥትና ቅጥረኞቹ ስለሆኑ::
ከዚህ ውጭ: “ፋኖ ደበደበኝ: የኣማራ ብልጥግናን ከክልሉ ኣባረረብኝ: ፋኖ ሰራዊቴን ስብርብሩን አውጥቶ የመዋጋት አቅሜን አመነመነብኝ: ስለዚህ WBO ለምን ዝም ይላል? ለምን አይረዳኝም?” የሚለውን የነሽመልስ አብዲሳን ለቅሶ WBO አይሰማም::
እንዲያውም ፋኖም ሆነ ሌላ ኃይል: ግፈኛውን የአብይኣህመድ ሥርዓት ለመጣልና ለህዝቡ መብት መከበር እና ዘላቂ እፎይታ ለማምጣት እስከ ታገለ ድረስ: የኦሮሞን ጨምሮ የሌሎች ሕዝቦችን ነፃነትና ፍትሓዊ እኩልነት እስካከበረ ድረስ: WBO ሊተባበራቸው መርህ ያስገድደዋል::
ከግፉኣን ሁሉ ጋር ቆመን: ዘር ኣጥፊና አፋኝ ሥርዓትን መዋጋት: ማንኮታኮትና መቅበር የህልውናችን ምክንያትና ታሪካዊ ጥሪያችን ነው::
አብይንከፋኖአናስጥልም!
ከገዳይናቀማኛሥርዓትጎንአንቆምም!
ለሽመልስየደቦጥሪ_ኣንመጣም!
ታሪካዊጥሪያችንለነፃነትናለእኩልነትለፍትሕናለሰብዓዊነትእንጂኣፈናናግድያንለማጀገንኣይደለም!
https://twitter.com/RArarssa/status/1861556163239964873?t=a_BuFIm_KtbEWlX4hZAdvw&s=19
