• Tue. Nov 24th, 2026

በሰሜን ኬንያ ውስጥ ስለሚከናወነው ዘመቻ (ከኦነግ – ኦነሠ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ)

Feb 5, 2025

የኬንያ ፖሊስ በማርሳቢት እና ኢሲዮሎ ግዛቶች (ካውንቲዎች) የወንጀል አካላትን ነቅሎ ለማጥፋት እንቅስቃሴ መጀመሩን የሚገልጹ ዘገባዎች ደርሰውናል።  የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) ስም ከነዚህ ተግባራት ጋር ተያያዞ የተገለፀ በመሆኑ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ለሚከተሉት ቁልፍ ነጥቦች ትኩረት መስጠት እንፈልጋለን፦

1ኛ. የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) የኬንያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ሙሉ በሙሉ ያከብራል። ከ95% በላይ የሚሆነው የደቡብ እዝ ሰራዊታችን በደቡባዊ ኦሮሚያ ውስጥ ወደ መኃል ገብቶ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ከ5% በታች የሆነው ሠራዊታችን ደግሞ ከኬንያ ድንበር ቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል። በእነዚህ አካባቢዎች የምናደርገው እንቅስቃሴም የኬንያን ሉዓላዊነት ያገናዘበና ያከበረ ነው።

2ኛ.  የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ)  ለቦረና እና ለሌሎች ወንድማማች የኬንያ ማህበረሰቦች ጸጥታ እና ደህንነት ያለው ቁርጠኝነት እንደ ሁልጊዜው የጸና ነው። የህዝቦቹን ሰላማዊ ህልውና የሚያናጉ የወንጀል ድርጊቶችን እንቃወማለን። አስፈላጊነቱ በአሁኑ ወቅትም ሆነ በማናቸዉም ግዜ በጋራ ድንበራችን ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከኬንያ ባለስልጣናት ጋር በትብብር ለመስራት ፈቃደኞች ነን።

3ኛ. ድንበር ተሻጋሪ የሆኑና እንደ አደንዛዥ እፅ፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የከበሩ ማዕድናት ዝውውር ላይ የተሰማሩ የወንጀል መረቦች በሁለቱም ድንበር በኩል የሚገኙ መሆናቸውን እናውቃለን። እነዚህ ህገወጥ ተግባራት የተቋቋሙት እና እንዳይጠፉ ድጋፍ የሚደረግላቸው በኢትዮጵያ መንግስት የጦር ሰራዊት እና የደህንነት መሥሪያ ቤቱ የስለላ አገልግሎት ከፍተኛ አባላት ሲሆን ህጋዊ የባንክ የገንዘብ ዝውውር መስመሮችን ጭምር ይጠቀሙ ዘንድ ለዚህ ወንጀል ድርጊታቸው ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥሮላቸዋል። በማናቸውም አጋጣሚ ማንኛውም የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባል እነዚህን በመንግስት የሚደገፉ ወንጀለኛ የኢትዮጵያ ገዢ ቡድን ጦር አበጋዞች እና የኢትዮጵያ ደህንነት መሥሪያ ቤቱን ሲረዳ ወይም ከለላ ሲሰጥ ውይም በማናቸውም ሆኔታ ተሳትፎ የተገኘ ካለ አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን።

4ኛ. የኬንያ ፖሊስ በሚወስደው የዘመቻ እርምጃ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና የኢትዮጵያው ገዢው ቡድን በተደራጀ ወንጀል ውስጥ ካለው ተሳትፎ ትኩረት ለማስቀየር በሚጥሩ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንዳይታለሉ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን። የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን የሚያደርገው፣ በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ላይ ርካሽ የህዝብ ግንኙነት ዘመቻን ለማካሄድ ሲሆን በራሱ መዋቅርና ተባባሪዎቹ ውስጥ ባሉ እውነተኛ ወንጀለኞች ላይ ትኩረት እንዳይደረግ አቅጣጫ ለማስቀየር በሎ ለዚሁ ግብዓት እንዲሆነው የፈጠራ ትርክቶችን ለመፍጠር ሊሞክር  እንደሚችል መገንዝብ ያስፈልጋል። በመሆኑም ትክክለኛ ወንጀለኞች በሌሉበት ቦታ ላይ ወንጀለኞችን መፈልግ ለእውነተኛ ተጠያቂዎች ከለላ ከመስጠት ያለፈ የተፈለገውን ውጤት አያስገኝም።

5ኛ. የኢትዮጵያ ገዥ ቡድን ተቃውሞን ለማፈን በተለይም በመላ ሀገሪቱ እያደገ የመጣውን ተቃውሞ ለማስቆም በሚያደርገው መፍጨርጨር ጎረቤት ሀገራትን ጎትቶ ወደ ውስጣዊ ግጭት እንዲገቡ ያደረገ የቅርብ ጊዜ ታሪክ አለው። ኬንያ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ በሚያስደንቅ ሆኔታ ገለልተኝነቷን አስጠብቃ መቆየቷን ብንገነዘብም፣ የኬንያ ባለስልጣናት በአሳሳቾችና፣ በተራ የአገር ክህደት ወንጀል በሚታወቁ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እንዳይሳሳቱ እናሳስባለን። ኬንያ ከሁሉም አካላት ጋር ሚዛናዊ እና ገንቢ የሆነ ግንኙነት በማድረግ ሰላምን በማጎልበት ለቀጠናው መረጋጋት የተለመደውን ትብብር እንድትቀጥል እንጠይቃለን። 

የኦነግ-ኦነሠ ከፍተኛ ዕዝ
የካቲት 4፣ 2025

Leave a Reply