• Wed. Sep 23rd, 2026

የውሸት የሰላም ዲስኩር፣ እውነተኛ ቀውስ፡ የአብይ አህመድ አዲስ የጦርነት ድግስ (የኦነግ-ኦነሠ መግለጫ)

Nov 11, 2025

ጥልቅ የፖለቲካ መገለል፣ የወታደራዊ አቅም መመናመን እና የኢኮኖሚ ውድቀት የገጠመው የአብይ አህመድ የብልጽግና (Phantom) ፓርቲ (PP) ቡድን ዳግም ወደ ለመደው የተሳሳተ መረጃ የማሰራጨቱ፣ የውክልና ጥቃቶች እና በሃይማኖት/በማንነት ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች እኩይ ተግባሮቹ ተመልሷል። በቅርብ ቀናት ውስጥ፣ አገዛዙ “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ከብልጽግና ፓርቲ ጋር በድብቅ ድርድር ውስጥ ገብቷል” የሚል የሀሰት ወሬ አሰራጭቷል። ይህ የፈጠራ ወሬ በኦሮሚያ ውስጥ ለወራት በዝቅተኛ ደረጃ ባሉ “በወንድማማቾች መካከል ጠመንጃዎችን ጸጥ ማድረግ” በሚል የተካሄደ የካድሬ ፕሮፓጋንዳ ተከትሎ ሲሆን፣ ይህም ቀደም ሲል በሚያዝያ ወር የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ካስጠነቀቃቸው የአገዛዙ እኩይ ስራዎች አንዱ ነው። እንዲህ ዓይነቱ የተሳሳተ መረጃ አዲስም ያልሆነ፣ በአጋጣሚም የተከሰተ አይደለም። ይህ አብይ የተቃዋሚ ሀይሎች እንቅስቃሴዎችን ቅቡልነት እና ህዝባዊ ድጋፍ ለመቀማት የሚያደርገው ሌላ ከንቱ ሙከራ ነው። ከልምድ እንደምናውቀው፣ ማታለልን እና ሁከትን እንደ አገዛዝ መሳሪያ አድርጎ ከሚጠቀም ሰው ጋር ዘላቂ የሆነ መፍትሔ መፍጠር አይቻልም።

ሌላው ተመላልሶ በአብይ ጥቅም ላይ የዋለው “ፖለቲካዊ መሳሪያ” የብሄር/ሀይማኖት ክፍፍል ነው። አገዛዙ ባለፈው አመት በጅማ እና በአርሲ አከባቢዎች ከፍተኛ ሁከት መቀስቀስ ባለመቻሉ፣ በቅርቡ በኦሮሚያ በሚገኙ የውክልና ግጭት ታጣቂ መዋቅሮቹ አማካኝነት በአርሲ ዞኖች በሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ማህበረሰቦች ላይ ጥቃት ፈጽሟል። በተመሳሳይ መልኩ አብይ በመላ አገሪቱ እሳት አቀጣጣይም አጥፊም ሆኖ ለመስራት ማቀዱን የሚያመለክቱ ተመሳሳይ የውክልና ጦርነት ተሳታፊ ወኪሎች በቅርቡ በአማራ እና በትግራይ ተፈጥሯል።

አብይ “የኦሮሞ ፓርቲ/መንግስት” ነኝ በሚል በተደጋጋሚ የመዘዘውን የብሄር ካባ/ካርድ ሀሰተኛ ትርክት ህዝባችን በሚገርም አኳኃን አልተቀበለውም። ይህ በህዝባችን የታየው ብስለት እና ንቃት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። በፅናት መቆም እና ከእንቅስቃሴያችን እውነተኛ መሪዎች ጋር በመተባበር መስራታችሁን ቀጥሉ። በኦሮሚያ እና ከዚያም ባሻገር፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ መርህ ያነገቡ ተቃዋሚ መሪዎችን እና በብልጽግና አገዛዝ ውስጥ ያሉ የህዝብ ተቆርቋሪነት ያላቸው ተዋናዮችንም ጭምር በማሰባሰብ ጠንካራ የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይል ብቅ ብሏል።

ስለዚህ አለም አቀፉ ማህበረሰብ በፍጥነት እርምጃ መውሰድ አለበት። ሀገሪቱ አብይ
በፈጠረው ሌላ የጥፋት አፋፍ ላይ ትገኛለች። ኢኮኖሚው እየወደቀ፣ ጦር ሰራዊቱ በመበታተን ላይ ባለበት እና ዲፕሎማሲው ወድቆ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ባለበት ሆኔታ፣ አብይ አህመድ፤ አሉታዊ ውጤቱ በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ብቻ የማይወሰን አዲስ ጦርነት ለመቀስቀስ ተዘጋጅቷል። ይህ ሁኔታ ከረጅም ጊዜ በፊት የታወቀ ቢሆንም፣ አሁን ባለው ሆኔታ በዝምታ ማለፉ የሚያስከፍለው ዋጋ የሚለካው በህዝባችን ህይወት ላይ በሚያመጣው ጣጣ ብቻ ሳይሆን በቀጠናው በሚፈጥረው አለመረጋጋትም ጭምር ነው።

የኦነግ-ኦነሠ ከፍተኛ ዕዝ

ታህሳስ 7 2025

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading