“ኦሮሚያን ለማፍረስ የሚከፈል መስዋዕትነት ኦሮሚያን ለመገንባት ይዋል”
የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ ጥሪ
የኦሮሞ ነፃነት ትግል በታጋዮች ደምና አጥንት እዚህ ደረጃ ደርሷል፤ የኦሮሞ ነፃነት ትግል ግቡ የሀገር ባለቤትነት እና ነፃነት እንደሆነ ይታወቃል፤ የኦሮሞ ልጆች የአሮጌው ሥርዓት ጠባቂዎች በመሆን የኦሮሞን መንደር እያቃጠላችሁና እያወደማችሁ ያላችሁ ወደ ኦሮሞ ህዝብ ትግል እንድትቀላቀሉ አጥብቀን እናሳስባለን፤
በኢምፓየር ውስጥ የሚገኙ ጭቁን ብሄር ብሄረሰቦች ሥርዓቱን ለመገልበጥ ከትንሽ እስከ ትልቅ ከብሄራቸው ታጋዮች ጋር እየተቀላቀሉ ይገኛሉ፤ በተለይ በሥርዓቱ ሥር ባሉት የክልላቸው ልዩ ኃይል መከላከያ እና ፌደራል ፖሊስ ያሉ ወደ ብሄራቸው ታጋዮች እየተቀላቀሉ ስሆን ታሪካችፕውን ከማቆሸሽና ከማጠልሸት እየታደጉ ነው፤ እኛ የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ(QBO) በጠላት ወረዳ ቆማችሁ የምትገኙ የወጣችሁበት ህዝብን እየበደላችሁና እያሠቃያችሁ ያላችሁት የእሮሞ ልጆች ከነገ ታሪክ ተጠያቂነት እራሳችሁን እንድታድኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤
የኦሮሞ ልጆች በመከላከያ በፌደራል ፖሊስ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የሥርዓቱ ጠባቂ እና ሚሊሻ ሆናችሁ አውቃችሁም ይሁን ሳታውቁ ለዚህ ነፍሱ ለመውጣት በመፈራገጥ ላይ ላለ ሥርዓት ብላችሁ የእሮሞን መንደርና እያወደማችሁ ያላችሁ ከዚህ አጸያፊ ድርጊታችሁ ተቆጥባችሁና ተመልሳችሁ ከኦሮሞ የሀገር ባለቤትነት እየጠየቀ ላለው ትግል እንድትቀላቀሉ አጥብቀን እናሳስባለን፤
እናንተ ከባለፈው አስቀያሚ ታሪክ ተምራችሁ የምትወዳችሁን ኦሮሚያ የምትገነቡበት ጊዜ አሁን መሆኑን አውቃችሁ በአከባቢያችሁ የሚንቀሳቀሰውን የኦሮሞ ነፃነት ጦር እንድትቀላቀሉ አጥብቀን እናሳስባለን፤
ጓዶቻችሁ ለጠላት መሣርያ መሆንን ትተው ወደ ኦሮሞ ነፃነት ትግልና የኦሮሞ ነፃነት ጦርን በመቀላቀል ላይ ያሉት የሚበረታታና የሚደገፍ ነው፤ የአባቶቻችን መንደር እናንተ ባላችሁበት ጦር ነው ክብር ያጣው ክብር የሚያገኘውም በእናንተ እንደሆነ እናሳስባችኋለን፤ በመጨረሻም የአማራ ኃይሎች የሥርዓቱ መውደቅ ሲያስደነግጣቸው ድንበር በመሻገር ህዝባችንን ከመንደሩና ከመሬቱ በማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል እየሠሩ በመሆኑ የጠላት መሣሪያ ታጥቃችሁ ጠላትን አቅም እየገነባችሁ መሆኑን አውቃችሁ ድንበር ተሻግሮ የመጣን ጠላት ከኦሮሚያ ላይ ለመመከት ወደ ኦሮሞ ነፃነት ትግል እንድትቀላቀሉ በድጋሚ አጥብቀን እናሳስባለን፤
መላው የኦሮሞ ህዝብ ማወቅ ያለበት አሁን የኢምፓየሪቷ ላይ እየሄደ ያለው ግጭት ሲያስተዳድሩና እያስተዳደሩ ባሉት መሀከል ያለውን በተመለከተ፦
የመንግሥቱ ካድሬዎች ውሸት የሆነውን እውነት በማስመሰል ህዝባችንን በማደናገር የእሮሞ ህዝብ በማይመለከተው ጦርነት አቅሙንና ሀብቱን እንዲያፈስበት እየቀሰቀሱ እንደሆነ ይታያል፤ ስለሆነም የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ(QBO) ለመላው ኦሮሞ ህዝብ “ምንም በማይመለከትህ የትኛውም ጦርነት ውስጥ ልጆቻችሁን ሀብትህን በማቀብ የህግ የበላይነትን በማስከበር በሚል በቤትህ ሚገልህን ጠላት ከልክል” በማለት መልዕክቱን ያስተላልፋል፤
“ኦሮሚያን ለማፍረስ የምታፈሰውን ደም ኦሮሚያን በመገንባት ላይ አውለው”
ድል ለኦሮሞ ህዝብ
የኦሮሞ ነፃነት ቄር(QBO)
ፊንፊኔ ነሀሴ 30,2022


