እሁድ ጥር 28 ቀን 2024 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ስዓት ጀምሮ በኦሮሚያ የታወጀው የገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እገዳ ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ይዟል።
የኦሮሞ ማህበረሰብ የቄሮን ህዝባዊ ተቃውሞ መግለጫን ተከትሎ ተግባራዊ በማድረግ ሱቆችን በመዝጋት ፣ ተሽከርካሪ በማቆም እና እንቅስቃሴውን በመገደብ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በዚህ ምክንያት ይህ ህገወጥ የብልፅግና ጨቋኝ እና አፋኝ አገዛዝ በነቀምቴ የኢንተርኔት ግንኙነትን እስከማቋረጥ ድረስ ያሳደረው ተጽእኖ የማህበረሰባችን ጥንካሬ እና የተቃውሞ ብቃት ያስመሰከረ ነው።
የብልፅግና ቡድን የህዝቡን ተቃውሞ በመፍራት በኦሮሚያ ውስጥ በየቦታው ብዙ ወጣቶችን፣ ሹፌሮችን እና ስራ ፈጣሪዎችን አስሯል። እኛ እንደ ኦሮሞ ነፃነት ቄሮ ኮሚቴ ለገበያ አድማ እና የመንገድ መዘጋት መግለጫ ስኬት እንዲሁም ለህብረተሰባችን አንድነት እና አብሮነት ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን።
በዚህ ስራ ላይ የስርዓቱን ጫናዎች፣ ክፍተቶች እና ድክመቶችን ተምረናል።
ከዚህ አዋጅ አተገባበር አንፃር ካጋጠሙ ጥቃቅን ድክመቶች እና ህብረተሰባችን የብልፅግና አገዛዝ በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማጥፋት ያለውን ፍላጎት ተምረናል። የአዋጁ ድል አበረታች ነው። በህዝባዊ እምቢተኝነቱ ያለ እረፍት ለተሳተፉ ወገኖቻችን እና ጥሪውን ሰምተው ተግባራዊ ላደረጉ ወገኖቻችን ሁላ ምስጋናችን የላቀ ነው።
ዛሬ ጥር 2 ቀን 2024 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የሰአት እላፊ ክልከላው የሚነሳ ሲሆን ህብረተሰቡም ከነገ ጠዋት ጀምሮ መደበኛ እንቅስቃሴውን መቀጠል ይችላል።
የሚከተሉት በገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እገዳ የተፈቀዱ ናቸው።
➢ ሱቆች ክፍት ናቸው።
➢ ምግብ ቤቶች
➢ የህዝብ ስራዎች
➢ ባንኮች
➢ ትምህርት ቤቶች
➢ ወደ ኦሮሚያ እና ፊንፊኔ የሚወስደው መንገድ ክፍት ናቸው።
➢ ሸቀጣ ሸቀጦች ከፊንፊኔ ወደ ኦሮሚያ ሊጓጓዙ ይችላሉ።
እስካሁን በእገዳ ስር ያልሆኑ ኩነቶች ሁላ ተፈቅደዋል።
ቀሪዎቹ በዚህ አዋጅ የተገደቡ አልያም (ያልተፈቀዱት):
➢ የቀንድ ከብቶች ፣ እህል፣ በግ፣ ፍየል፣ ዶሮ ከኦሮሚያ ወደ ኦሮሚያ ዋና ከተማ ፊንፊኔ ማጓጓዝ አይቻልም።
➢ የኦሮሞ ነጻነት ቄሮ ኮሚቴ ባለንብረቶች በዚህ አዋጅ ሽፋን የተሽከርካሪዎችን ዋጋ በህዝብ ላይ ከመጫን እንዲቆጠቡ በጥብቅ ያሳስባል።
ህዝባዊ ንቅናቄው አገዛዙን አስወግዶ ነፃነቱን እና ሏአላዊነቱን እስካላረጋገጠ ድረስ ጨቋኙን ስርዓት በመቃወም የሚያደርገው ትግል ይቀጥላል። የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት በኦሮሚያ ላይ ሙሉ ነፃነት፣ ሉዓላዊነት፣ የሌላ ብሄር ብሄረሰቦች መብት የተከበረበት እንዲሆን እንጂ የተጭበረበረ ስራአት እንዲዘረጋ አይደለም። የህዝብ ጥያቂያቄ አሁኑንም በአስቸኳይ እንዲመለስ እናሳስባለን።
ከኦሮሞ ነጻነት ቄሮ!
የካቲት 2, 2024 ዓ.ም!
ፊንፊኔ, ኦሮሚያ!
ድል ለኦሮሞ እና ለጭቁን ህዝቦች!
