መጋቢት 26/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በሰሜን ኦሮሚያ፣ ወሎ ዞን፣ ጂሌ Dhuሙጋ ወረዳ ሥር በሚገኙ እንደ ዲሪች፣ አላላ፣ በርሲሳ፣ ጉባ ዋጩና መካና አጣዬ ቀበሌዎች ዉስጥ በፋሺስቱ የአቢይ አህመድ ሃይል እየተደገፈ ያለዉ ጽንፈኛው የአማራ ሃይል ፋኖ የከፈተው ጥቃት እንደቀጠለ ነዉ። በነዚህ ቀበሌዎች የኦሮሞ ህዝብ መኖርያ ቤቶች በጽንፈኛ ሃይሉ ሌሊት በእሳት መዉደማቸውን ምንጮቻችን ዘግበዋል።
በዚሁ በሰሜን ኦሮሚያ፣ ጂሌ Dhuሙጋ፣ የአማራው ጽንፈኛ ሃይል በኦሮሞ ህዝብ ላይ በከፈተዉ ግልፅ ጦርነት የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 20 ንጹሃን ዜጎች መቁሰላቸዉን ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
በዚህ የአማራ ጽንፈኞች ዘመቻ አካል በሆነዉ የወሎ ኦሮሞን ከመሬቱ ላይ የማጥፋት ህልም አላሚዎችና የዚህ እኩይ ምግባር ግምባር ቀደም ተሳታፊዎች ጽንፈኛው የአማራ ፋኖ፣ እና የአማራ ልዩ ኃይል ሲሆኑ፤ በተጨማሪም መንግስት ነኝ ባዩ የብልፅግና መዋቅርም ድጋፍ እያደረገና እያስታጠቀ መሆኑን ህዝቡ ይናገራል።
ላይነጋ አይመሸምና የኦሮሞን ሕዝብ አጥፍተን ንብረቱንና ሐገሩን እንወርሳለን የሚሉትን የህልም እንጀራ አላሚዎችን አደብ ግዙ እንላለን ።
ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!
