መጋቢት 30/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኦሮሞ ህዝብ ክንድ እና ጋሻ የሆነው የደቡብ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በዝርፊያ፤ አስገድዶ በመድፈር እና በጅምላ ግድያ የኦሮሞን ህዝብ እያሰቃየ ያለዉ የብልፅግና ኃይል ላይ መጋቢት 14/2024 በምዕራብ ጉጂ፣ ቡሌ ሆራ ወረዳ፣ በጋሌ መጋዳ ቀበሌ በወሰደው እርምጃ አስራ ሰባት የብልፅግና ጦር አባላትን ወዲያውኑ ሲገድል አስራ አንዱን መትረፍ በማይችሉበት ደረጃ አቁስሏል።
በትጥቅ በኩልም አንድ ፒኬኤም ከ670 ጥይቶች ጋር፣ አምስት ኤኬኤም ከ353 ጥይቶች ጋር አራት የነብስ ወከፍ ትጥቆችን እና የተለያዩ አልባሳትንና ቁሳቁሶችን በማስፈታት ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ዓላማ እንዲውልገቢ አድርጓል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚወስደውን እርምጃ እስከ ነፃነት እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!
