መጋቢት 28/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በፖለቲካ ትግል ውስጥ ምንም ተሳትፎ የሌላቸው ንጹሃን ዜጎችን በመግደል ፍርሃትን በህብረተ፡ሰቡ ዉስጥ አስፍኖ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚፈልገው የብልጽግና ሥርኣት፣ በመላው ኦሮሚያ ነዋሪዎችን (ኦሮሞዎችን) በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉን ቀጥሎአል። በዚሁ መሰረት መጋቢት 16/2024 ጠዋት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ቀርሳ ማሊማ ወረዳ፣ አዋሽ ፋልቴ ቀበሌ፣ የ5 ልጀች አባት የሆኑትን አዛውንት እና የሐገር ሽማግሌ ኦቦ ቸሩ ዳdhi የተባሉትን የኦሮሞ ተወላጅ ከቤታቸው በመያዝ፣ በዚሁ ዕለት ሌሊት መግደላቸው ታውቋል።
በዚሁ ዞን ቶሌ ወረዳ፣ ወሰርቢ ሚጊሪዲ ቀበሌ፣ በትምህርቱ የላቀ ነጥብ ማስመዝገቡ የሚነገርለትን ሰቦና ኩማ የተባለን ተማሪ የአብይ አህመድ መራሹ ሰራዊት ከሚማርበት ከላሊሴ ትምህርት ቤት ይዘውት ለ5 ቀናት በጦር ካምፓቸው አስረው ካሰቃዩት በኋላ፣ “ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ትሰልላለህ” በሚል ሰበብ መጋቢት 16/2024 ከታሰረበት በማወጣት መግደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ለሚዲያችን ገልጸዋል።
የኦሮሞ ታዳጊ ልጆችን እና የሐገር ሽማግሌዎችን ጭካኔ በተሞላበት መግደል የኢምፓየሪትዋን ውድቀት ያፋጥነዋል እንጂ የኦሮሞን ሕዝብ ማንበርከክ አይችልም።
ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!
