ሚያዚያ 14/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
መደበኛ ስራውን ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር ጦርነት ያደረገው የፋሺስቱ አብይ አህመድ የብልጽግና ቡድን ያለማቋረጥ አዳዲስ ወታደሮችን በመመልመል ላይ ቢሆንም፤ ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድወደ ጦር ግምባር ከሚላኩት በሞት፣ በምርኮኛነትና ስርዓቱን በመክዳት የሚቀነሱት ወታደሮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ይገኛል። ይህም ሁኔታ ፋሺስት አብይን እና የብልጽግና ቡድኑን ትልቅ ድንጋጤ ዉስጥ ከቶአቸዋል።
ይህንን በቁጥር የመቀነስ ችግር ለመቅረፍ፣ በመላው ኦሮሚያ የድሆች እናቶችን ልጆች ያለፍላጎታቸው በማስገደድ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከሎች በመላከ ይገኛሉ። በዚህም መሰረት መጋቢት 25/2024 በአርሲ ዞን፣ አዳባ ከተማ ውስጥ ብቻ 210 ሰዎች ያለፍላጎታቸው ተይዘው ወደ ውትድርና ስልጠና ትወሰዳላችሁ ተብለው በአዳባ ከተማ አስተዳደር ዉስጥ በአፈሙዝ እየተጠበቁ እንደሚገኙ አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ከአካባቢው ነዋሪዎች ዜናውን አጠናቅሮአል።
ግማሾቹን ደግሞ የግል ስራቸውን እየሰሩ ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳደሩትን ያለምንም ምክንያት ከቤተሰቦቻቸው ቤት በማባረር ልጆችንና ቤተሰቦችን ያለፈቃዳቸው እያለያዩ ይገኛሉ። ይህንንም አስጸያፊ ድርጊት በማመቻቸትም ሆነ በመፈጸምላይ የሚገኘው የማፍያው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆነው ኦቦ ሴፉ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ከዚህም በላይ የፀጥታና የአስተዳደር ቡድኑን ከወረዳ እስከ ቀበሌ በመዘርጋት ከመጋቢት 23/2024 እስከ መጋቢት 25/2024 በመንገድ ላይ የሚሄዱ ሰዎችን በማደን ሲይዙ ለሶስት ቀናት ቆይተው ነበር። አሁንም ወደ ውትድርና ስልጠና ሊወስዱዋቸው በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ከአካባቢው ነዋሪዎች መረጃ አግኝቷል።
እንግዲህ አቢይ አህመድ የኦሮሞን ሕዝብ ቁጥር በመቀነስ፣ የተወሰኑ የትውልድ እርከንንም በመቅጨት እና ሕዝቡን አንበርክኮ ለመግዛት በእቅድ እየሰራ መሆኑን ከዚህ የበለጠ መረጃ የሚያስፈልግ እይመስለንም። የኦሮሞ ሕዝብ ከምን ጊዜም በላይ አንድነቱን አጠናክሮ ይህንን ፋሺስታዊ ስርዓት ከላዩ ላይ አሽቀንጥሮ መጣል ይጠበቅበታል።
