ሚያዚያ 10/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ፋሺስቱ የአብይ አህመድ መራሹ ብልፅግና ጦር ቡድን የኦሮሞን ቄየ ከባድ ሀዘን እንዲላበስና የኦሮሞ እናት ህይወትም ክብር አጥቶ ከነልጆቿ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ ደሙዋ እንደ ጅረት ዉሃ እንዲፈስ የሚደረግበት ጊዜ ላይ እንገኛለን።
መጋቢት 29/2024 በምሥራቅ ሸገር ዞን ፈንታሌ ወረዳ፣ ቆላ ቀበሌ በሳራ መንደር የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን እንፈልጋለን በሚል ስም ወደ ቀበሌው የተሰማሩት የብልጽግና ጦር ቡድን አንድ እናት እና ሁለት ልጆቿን በጥይት ደብድበው መግደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።
ከልጆችዋ ጋር የተገደለችው እናት ሀሎ አሊ ወዳይ የምትባል ሲሆን የተገደሉት ልጆችዋ ደግሞ ሞሚና አሊ ሰይድ እና መሮ አብዲ ሀሰን የሚባሉ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።
ይህች እናት የፋሺስት አብይ አህመድ ጦር ልጆችዋን ከብቶች በሚጠብቁበት ልዩ ስሙ ዱግዳ ጀቢ በተባለ ስፍራ ላይ መግደላቸውን ሰምታ እያለቀሰች የልጆቿን ሬሳ ለማንሳት ስትሮጥ እሷ ላይም በመተኮስ እንደገደሏት ታውቋል።
የኢምፓየሪትዋ ገዢ ፋሺስት አቢይ አህመድ ጭካኔ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እራሱ ባደራጃቸው ታጣቂዎች እየተፈጸመ ያለው ድርጊት በዓለም ታርክ ተፈጽሞ የማያዉቅ እና በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ የህዝቡን መጻኢ ዕድል አሳሳቢ ያደርገዋል።


