• Sun. Mar 15th, 2026

በቡኖ በደል ዞን፣ ዳቦ ሃና ወረዳ የብልጽግና ማፍያው ቡድን የኦሮሞን ህዝብ ንብረት መዝረፍን እና ቤቱን ከነንብረቱ በእሳት ማውደምን ቀጥሏል

Apr 14, 2024

ሚያዚያ 14/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ፋሺስት አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ኢምፓየር ውስጥ አምባገነናዊ አገዛዝን አዳብሮ የኦሮሞን ህዝብ ማሰሩን፣ በእስር ቤት ማሰቃየቱን፣ ንብረቱን መዝረፍ እና ቤት ንብረቱን በእሳት ማውደሙን ቀጥሏል። ይህንንም ተግባር የሚያካሂደው የኦሮሞን ህዝብ የበይ ተመልካች ለማድረግ እና በገዛ ቄዬው ላይ ሁለተኛ ዜጋ አድርጎ ለመግዛት ነው።

መጋቢት 22/2024 በዳቦ ሃና ወረዳ በኢፋባስ ጮሬ ቀበሌ የፋሺስት አቢይ ሰራዊት ቡድን የሚከተለዉን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በኦሮሞዎች ላይ ፈጽመዋል፦

  1. ከአብደላ አብራሂም እና አሪፎ አህመድ ስድስት የቀንድ ከብቶችን
  2. ከጂያዶ ረሺድ አንድ የቀንድ ከብት ከነ ጥጃዋ የወሰዱባቸዉ ሲሆን፣
  3. ኦቦ ጃምቦ እና 
  4. ኦቦ ናስር ያሲን የተባሉ ግለሰቦችን ደግሞ ቤታቸዉን ከነንብረቱ በእሳት አንዳወደሙባቸው ታዉቇዋል።

እንደዚሁም የሚከተሉትን፦

  1. ሼክ ሙክታር፣
  2. መሀመድ አቡበከር፣
  3. ዮኒስ ጀማል፣
  4. ኡስማኤል አብዱራማን፣
  5. ሃምዛ ሞጋላ እና
  6. አደም ሙሜ

የተባሉትን የቀበሌዉ ነዋሪዎች ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሃሰት ዉንጀላ ከባድ ድብደባ እና ስቃይ እንደፈፀሙባቸው ምንጮች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት እና የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading