• Sat. May 9th, 2026

በፊንፊኔ ከተማ የ18ኛ ክ/ከተማ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ በሃበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ላይ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ስም የ12 ሚሊዮን ብር ዘረፋ ለማድረግ ሙከራ ማድረጉ ተነገረ 

Apr 28, 2024

ሚያዚያ 28/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ጥላሁን ገዛኽኝ የተባለው በፊንፊኔ ከተማ አስተዳደር የኮልፌ ቀራኒዮ (18) ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዥ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ስም በሃበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ላይ የዘረፋ ወንጀል ሊፈጽም ሲል ተደርሶበታል። ይህ አስመሳይ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በመምሰል እና በማስፈራራት የሃበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካን 12 ሚሊዮን ብር እንዲከፍለው መጠየቁ ታውቋል።

ይህ የፖሊስ አዛዥ በሆለታ ከተማ የጎሮ ቄረንሳ ቀበሌ ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የባንክ ሠራተኛ ከሆነው ስዩም መንገሻ ከተባለ ግለሰብና እንዲሁም ከሌሎች አራት ፖሊሶች ጋር በመሆን በኦሮም ነፃነት ሰራዊት ስም በሃባሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ላይ ዘረፋ ለማድረግ የተሳተፈ መሆኑም ተገልጿል።

የ12 ሚሊዮን ብር ጥያቄ በነዚህ ዘራፊዎች ለሃበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሲቀርብ የፋብሪካው ሃላፊዎች ይህንን የጠየቁት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እንዳልሆኑ በመረዳት “እኛ አሁን 12 ሚሊዮንብር የለንም” በማለት ለሌላ ቀን ቀጠሮ ይዘው የሸኙዋቸው ሲሆን በተያዘዉም ቀጠሮ መሰረት እኩይ ድርጊት ፈጻሚዎቹ ቀጠሮ አክብረው ሲመጡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ተደርጎአል። እነዚህ ሌቦች በአሁኑ ሰዓት በምዕራብ ሸዋ ዞን በወልመራ ወረዳ ታስረው እንዳሉ ከሆለታ ከተማ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና ቡድን ሌቦችንና ዘራፊዎችን በማደራጀት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ስም ለማጠልሸትና ለማስጠላት የኦሮሞ ህዝብንና ድርጅቶችን በማዘረፍ ላይ እንዳሉ አንድ ለደህንነቱ ሲባል ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የሆሎታ ፖሊስ ባልደረባ በተጨባጭ መረጃ አስረድቶአል።

ይኸው የማስረጃ ምንጫችንም በተጨማሪም የኦሮም ነፃነት ሰራዊት የኦሮሞ ከኢምፓየሪትዋ እና አምባገነኑ መሪ የኦሮሞን ህዝብ ነፃ ለማውጣት ራሱን ችሎ የሚታገል እንጂ እንዲህ ዓይነት ወንጀል እንደማይሠራ እናውቃለን፤ ይኸውም የማጭበርበር መዋቅርና ህዋስ (ሴል) በማቋቋም እና በማደራጀት ሌብነትን በመዘርጋት ህዝባችንን እያዘረፈ ያለው የብልፅግናው የዘረፋ ቡድን መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል። ሕዝባችንም ግማሹ ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በመምሰል ግማሹ ደግሞ ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ስም እየዘረፈ ያለው መንግስት ተብዬው የብልፅግና ቡድን መሆኑን ማወቅ አለበትም ብሏል።

በተጨማሪም ይዞ ያሰረውም ሆነ የታሰሩትም ሌቦች ናቸው አብረው ሲበሉም ነበር። በቅርቡም ይፈታሉ እነሱም ብዙ በጥቅም ላይ ያልተጋጩ ነገር ግን የኦሮሞን ሕዝብ እየጋጡ እንዳሉና እንደተሰማሩም ጨምሮ ገልጿል።

በኢምፓየሪትዋ ዉስጥ ላላችሁ ብሔር ብሔረሰቦች የኦሮሞ ሕዝብ የነፃነት ትግል እውነታን እና አላማን በጥሞና ተከታተሉ እንላለን።

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading