ሚያዚያ 27/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኦሮሞ ህዝብ ክንድ እና ጋሻ የሆነው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በጠላት ላይ የሚወስደውን ጠንካራየጥቃት እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚሁ መሰረት ሚያዚያ 2/2024 ጀግኖቹ የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ የመደወላቡ ጭብራ በምስራቅ አርሲዞን በሺርካ ወረዳ፣ ገለቤ አመጃ ቀበሌ ልዩ ስሙ አንጆ በሚባል ስፍራ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን በማሰሰ ስም ተሰማርቶ ሰላማዊውን ህዝብ ሲያሰቃይ እና ሲዘርፍ በነበረው የብልፅግና ጦር ላይ በወሰደው በደፈጣ የማጥቃት እርምጃ 10 የጠላት ሃይልን ገድሎ 14ቱን በማቁሰል በድል አጠናቋል።
ኦሮሚያ ሐገር ነበረች፣ ሐገርነትዋንም መልሳ ትጎናፀፋለች።
