ሚያዚያ 27/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኦሮሞ ህዝብን ከምድረገጽ የማጥፋት ዓላማ አድርገው እየሠሩ ያሉት የፋሺስት አብይ ብልፅግናታጣቂ ቡድኖች በአሁኑ ሰዓት በመላው ኦሮሚያ ከፖለቲካ ነፃ የሆኑ ኦሮሞዎችን ከመዝረፍ፣ በከባድ ድብደባም አካለ ስንኩላን ከማድረግ፣ ቤት ንብረታቸውንም እህልን ጨምሮ ከማቃጠልም እልፈዉ የኦሮሞን እንቁ ልጆች በገፍ ከእስር ቤት ሆነ ከወላጆቻቸው ጉያ እየወሰዱ ገድለው ለጅብመመገብ ከጀመሩ አመታት ቢያስቆጥሩም በአሁኑ ጊዜ ደግም ማንነታቸዉም እንዳይታወቅ ከትውልድ/ከመኖሪያ አካባቢያቸው አርቀው እኩይ ተግባራቸውን በመተግበር ላይ ይገኛሉ።
መጋቢት 23/2024 ቢርቢርሳ ጉዳ ሰቦሌ ቀበሌ ውስጥ
ለጥፋት የተሠማሩት የፋሺስት አብይ አህመድ ጦር ቡድኖች የሶስት ገበሬዎችን ቤት ከነንብረቱ እንዳጋዩት የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራትቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል። ይህም ጉዳት የደረሰባቸው በእድሜ የገፉ እና በፖለቲካ ምንም ሚና የሌላቸው መሆናቸዉን ምንጮቻችን ጨምረው ሲገልፁልን ግፈኞቹ ግን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትረዳላችሁ፣ ትመግባላችሁ ብለው ነው ቤት፣ ንብረትና ምግብ ያሳጡዋቸው። ስማቸውም፦
- ኦቦ ኢፋ ብርሀኑ
- ቃጫ አያኖ
- ኢፍታሁ ኮርቦ ናቸው።
ሚያዚያ 3/2024 መቂ ከተማ አስተዳደር ውስጥ
በእስር ቤት የነበሩ ሶስት ቄሮ እስረኞችን በምሽት በመኪና በመጫን የከተማዋ መውጫ ላይ ካደረሱዋቸው በኋላ በፋሺስት አብይ ገዳይ ጦር ቡድን በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በነጋታው፣ ሚያዚያ 4/2024 ጠዋት ከጅብ የተረፈውን አካላቸዉን ለመሰብሰብ ቢችሉም፣ ማንነታቸዉን ግን መለየት አለመቻላቸዉን ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።
በዚሁ ዕለት ምሽት እነዚሁ የፋሺስት አቢይ ብልፅግና የጥፋት ቡድኖች 01 ቀበሌ ውስጥ ክፉኛደብድበው የለቀቅዋቸው አባ ወራዎች፦
- ኦቦ ኢሮ ጎልጄ፣
- ኦቦ አያኖ ጃጎ፣
- ኦቦ ሞአታ ጃጎ እና
- ኦቦ ጃጎ ከኔን ይባላሉ።
የፋሺስት አቢይ ብልፅግና ለድብደባ፣ ዝርፊያ እና ግድያ ባሰማራቸው ቡድኖቹ በኩል፣ በምስራቅ ሸገር ዱግዳ ወረዳ በንፁሃን ኦሮሞዎች በተለይም አርሶ አደሮች ላይ የሚደረጉት ዘግናኝ ድርጊቶች እይተባባሱ ሄደዋል። ቄሮዎች በከተማም ሆነ በገጠር መንገዶች የመንቀሳቀስ መብታቸውን ማገት ከጀመሩ ውሎ አድረዋል።
ይኸው የፋሺስት ቡድን ሚያዚያ 5/2024 መቂ ከተማ ጊሪሳ ማዞሪያ በሚባለው ቦታ ላይ ሶስት ቄሮዎች ወደ ዕለት የስራ ቦታቸው እየሄዱ እያለ በመያዝ ከባድ ድብደባ ከፈጸሙባቸው በኃላ ጥለዋቸው ሄደዋል። እነኝህ ክፉኛ የተደበደቡ ቄሮዎች ጉታ ጂማ እና ባቲ አቡ ሲሁኑ መቂ ሆስፒታል ገብተዉ በህክምና ላይ ይገኛሉ።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት እና ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪም ብቻ ሳይሆን፤ የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”
