ሚያዚያ 25/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ኦሮሞን ከኦሮሚያ እናጥፋ በሚለው መርሆ ፋሺስት አብይ አህመድ ገዳዮቹን በተለያየ ረድፍ እያስታጠቀ ይገኛል። የዚህ እኩይ ዕቅድ አንዱ አካል ሚሊሽያዎችን ምንም ዓይነት የፓለቲካ ግንዛቤ እና የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ስነምግባርን ሳያስጨብጡ በማስታጠቅ ኦሮሚያ ዉስጥ የግል ቂም በቀላቸውን እንዲወጡ ማሰማራት ሆኖአል።
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ኦዳ ቡልቱም ወረዳ፣ በዴሳ ከተማ ቀበሌ 02 በቡርቃ ሚሶማ መንደር ዉስጥ የሚኖረው ሚሊሻ ሙሜ መጋቢት 27/2024 ኦቦ ጀማል ዩሱፍ የተባሉትን ግለሰብ በጥይት እቁስሎ በሞት እና በህይወት መካከል እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል። ሚሊሻ ሙሜና መሰሎቹ የታጠቁትን መሳሪያ ለቂም በቀል መወጫ ብቻ ሳይሆን የሕዝብንም ንብረት ለመዝረፍ እንደሚጠቀሙበት ይነገራል።
ፋሺስት አብይ ኦሮሞን በሁሉም አቅጣጫ አዳክሞ እንደ ባሪያ ለመግዛት ለሚያልመው የተለያየ ተግባርን እያካሄደ ስለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖዋል። በዚሁም መሰረት አርሶ አደሩን ባለፉት ሶስት አመታት ንብረቱን ከመዝረፍ፣ ቤት ንብረቱን በእሳት ከማውደምም አልፎ የቤት እንስሳዎቹንም ጨምር በጦር ሜዳ መሳሪያ እየገደለ ይገኛል።
ካለፉት አምስት አመታት ጀምሮ ኦሮሞ በማሳው ላይ እንደልቡ እንዳይንቀሳቀስም ታግዷል። ወደ ማሳው ሲሄድ የኦሮሞ ነፃነትን ልትጎብኝ ወይም ጎብኝተህ ተመለስክ በመባል ብዙዎች በመንገድ ላይ ተገድለው የጅብ እራት ሆነዋል።
እንዲህ ዓይነት ግፍ እየተፈጸመበት “አምርት ያልንህን ስንዴ ስላላመረትክ” ብሎ በመወንጀል የስንቱ አርሶ አደር እሸት ከማሳው እንደተነቀለበት ወይም በእሳት እንደጋየበት ቤቱ ይቁጠረው። እንደሌላው የኢምፓየሯ አካባቢ የኦሮሞ አርሶ አደር ለምርት የሚያስፈልጉት ግብዓት ማዳበሪያንም ጨምሮ የማግኘት እድሉ የመነመነ ሲሆን ከሁሉም በላይ ግን በጊዜው ለማይሰጠው ግብዓት (ማዳበሪያ) የቅድሚያ ክፍያ ካልከፈልክ እየተባለ ይገደዳል። በምድር ላይ ያለው እውነታ የኦሮሞ ህዝብ በአንድ ዓመት ውስጥ ቢያንስ ሶስት ጊዜ ግብር እንደሚከፍል አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ከህዝቡ ባገኘው መረጃ ተመስርቶ ሲዘግብ ነበረ።
ሚያዚያ 8/2024 በምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ኦዳ ቡልቱም ወረዳ፣ በዴሳ ከተማ ውስጥ የብልፅግና አስተዳደር (ካቢኔ) እና ታጣቂ ቡድኑ አብሮ በመሆን ዋቀሊ በተባለ ስፍራ ህዝቡን በመሰብሰብ ማዳበሪያ ከመውሰዳችሁ በፊት መጀመሪያ ገንዘብ ባንክ አስገቡ እንዳሏቸው አንድ ስብሰባውን የተሳተፈ አርሶ አደር ተናግሯል።
ይህ አርሶ አደር እንደሚለው የዘንድሮ የማዳበሪያ ዋጋ ከባለፈው ዓመት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ካቢኔዎቹ ሲናገሩ እንደነበረና የካቢኔዎቹ ዋና አላማም ሕዝቡን መዝረፍ መሆኑን ገልጾ ሕዝቡ ገንዘቡን ከመክፈሉ በፊት በጥሞና እንዲያስብ በማለት ምክሩን ለገሶአል።
በተልይም በአሁኑ ወቅት ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሲቀርብ ከነበረው ያልተመጣጠነ የምግብ ሜኑ ይባስ ብሎ የምግቡ መጠን የበለጠ እንደሚቀንስ ማሳሰብያዎች እየወጣ ባለበት ሰዓት መንግስት የእርሻ ምርት ግብዓትን ዶላር ከፍሎ ያስመጣል እና የሚያስፈልገውን የቅድምያ ክፍያ መክፈል ማለት ”የቆጡን አወርድ ብላ የብ ብቷን ጣለች” የሚለው አባባል እንዳይከሰት ጠንቀቅ ማለት አስፈላጊ ነው። ስነምግባር የሌለው መሪ ህዝቡን በስነምግባር ሊያንጽ አይችልምና ዉሎ ሳያድር የሚያቆመዉ የሕዝብ ማዕበል የሚያስፈልግበት ወቅት ነው እንላለን።
