• Sat. May 9th, 2026

በምስራቅ ሸገር፣ ቦሰት ወረዳ፣ ኦለንጪቲ ቀበሌ ዉስጥ ኦሮሞን በእስር ቤት ዉስጥ ማሰቃየት፣ አካል ጉዳተኛም ማድረግ እና ንብረታቸዉን መዝረፍ ተባብሶ ቀጥሏል

Apr 23, 2024

ሚያዚያ 21/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የፋሺስት አቢይ አህመድ ብልጽግና ሰራዊት ቡድን በኦሮሚያ ሰላማዊ ዜጎችን ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እያሰረ ከዚያም በኋላ ከእስር ቤት ወደ ወታደራዊ ካምፖች እያጋዘ ከባድ ድብደባ እና ስቃይ እያደረሰ ሰዎችን ለአካል ጉዳትም እየዳረገ ይገኛል።

መጋቢት 22ቀን 2024 እረፋድ ላይ የፋሺስት አቢይ የኢምፓየሪትዋ ታጣቂዎች ከየት እንዳመጧቸዉ የማይታወቅ አራት ግለሰቦችን ዲልዲላ በተባለ አከባቢ ወደሚገኘዉ የጦር ካምፕ አስገብተዋቸዉ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነና ጩኸታቸውም እንዳስጨነቃቸው የአካባቢዉ ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በምስራቅ ሸገር ቦሰት ወረዳ ኦላንጪቲ ከተማ መግቢያ ላይ የፋሺስት አብይ አህመድ ታጣቂና ዘራፊ ቡድን ተሽከርካሪዎችን በግድ በማስቆም 200 ብር ከእያንዳንዱ መንገደኛ እየሰበሰበ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል። እነዚህ ታጣቂዎች ምሽት ምሽት መንገደኛዉን እያስቆሙ ገንዘብ፣ ስልክ እና የአንገት ሀብልም እየዘረፉ እንዳስቸገሩ ምንጮቻችን አክለዉ ነግረዉናል።

ኦሮሞን በመዝረፍ፣ በማሰር፣ አስሮም በማሰቃየት በህሊናዉ የተከተበዉን የነፃነት ጥማት እና የነፃነት ትግል ከነፃነት በፊት ሊያስቆመው የሚችል ሃይል የለም።

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading