• Sat. May 9th, 2026

በምስራቅ ሐረርጌ፣ ደደር ወረዳ፣ ማረሚያ ቤት ታስረዉ ያሉ እስረኞችን ወደ ፍርድ ቤት ሳያቀርቧቸዉ ለረጅም ጊዜ እያሰቃዩአቸዉ ይገኛሉ

Apr 23, 2024

ሚያዚያ 21,2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

እንደሚታወቀዉ በብልጽግና ዘመነ መንግስት ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ከቤት የወጣ ኦሮሞን ከመንገድ እየተያዘ፣ “የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተልዕኮ አልህ” በሚል ሰበብ ማሰር፣ ማሰቃይት፣ እና መግደል እንደቀጠለ ነዉ። በግል ንግድ ተሰማርተዉ ከፊንፊኔም ሆነ ከሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች ወደ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ደደር ወረዳ፣ ሶቃ ከተማ በመጓዝ ላይ ያሉትን ሰዎች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተልዕኮ አላችሁ በማለት ወደ እስር ቤት እያጋዝዋቸዉ መሆኑን የእስረኞቹ ቤተሰቦች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስር ካዋሏቸዉ ሰዎች መካከል አህመድ አደም የተባለ ወጣት የፊንፊኔ ከተማ ነዋሪ እና ለግል ንግድ ወደ ወረዳዉ ሲጓዝ የነበረ ሲሆን፣ የፋሺስት አብይ ብልፅግና ቡድን ጦር ያለምንም ምክንያት “ፀጉረ ለውጥ” ነው በሚል ሰበብ ከባድ ድብደባ አድርሰዉበት እንደነበር አና ከበርካታ ቀናት ፍለጋ በኋላ መጋቢት 6/2024 በሶቃ እስር ቤት መገኘቱን ምንጮቻችን ነግረዉናል።

እንድዚሁ በዚሁ ወረዳ ለስራ ጉዳይ የተሰማሩ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች በዚሁ በሶቃ እስር ቤት ዉስጥ መኖራቸዉን ምንጮቻችን ተናግረዋል።

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading