• Mon. May 4th, 2026

ጉዳዩ: የአብይ መንግስት በአዲስ መልኩ ወታደራዊ ከበባ በኦሮሚያ መተግበር (የኦነግ-ኦነሰ መግለጫ)

Apr 28, 2024

በሚያሳዝን ሁኔታ እየተባባሰ የመጣው የጅምላ ቅጣት እርምጃ፣ ተስፋ በቆረጠው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት፣ በምዕራብ ኦሮሚያ አዲስ የከበባ እርምጃ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት እና ሸሪኮቹ በትግራይ ጦርነት መጀመሪያ ላይ ሙሉ ከበባን ስራ ላይ አውለው ነበር። በተመሳሳይ መልኩ ከበባን በከፊል የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ላለፉት አራት ዓመታት ያለማቋረጥ ቢሞክርም፣ የመከላከያ ሰራዊቱ በትግራይ አካባቢ እንዳደረገው በሙሉ አፈና የህዝብን ህልውና ለአደጋ አጋልጦ ማንበርከክ አልቻለም። ምክንያቱም የሃገሪትዋ አብላጫ የተፈጥሮ ሃብት ለምርት የሚቀርበው በአብዛኛው የሚገኘው ከኦሮሚያ በመሆኑ ነው። የብልፅግና መንግስት ስለ ሕዝቡ ስቃይ ምንም የማይገደው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከበባን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም የራሱን ግሮሮ እንደመዝጋት ስለሚሆን ሙሉ ከበባን ተግባራዊ ማድርግ አልቻለም። በተጨማሪም የኦሮሚያ ግዝፈት እና ጂኦግራፊያዊ ማእከላዊነት ለሙሉ ከበባ ምቹ አልነበረም።

ስለሆነም በተለየ ሁኔታ የተጠና ከበባ በምዕራብ ኦሮሚያ እስከ ምዕራብ ሸዋ ድረስ መተግበር ተጀምሯል። ይህም በመከላከያ ሰራዊት እና በአከባቢው ካድሬዎች የቀናጀ ሲሆን፣ አላማውም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት ቤተሰቦችን ለሞት፤ ለስቃይ እና ለስደት መዳርግን ኢላማ ያደረገ ነው። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባል ቤተሰቦች፣ አባት፣ እናት እና ደጋፊዎች በሙሉ፤ የጤና አገልግሎት፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት፣ የፍትህ አገልግሎት እና ማናቸዉም የማህበረሰባዊ አገልግሎቶችን እንዳይጠቀሙ ታቅበዋል። ማዕቀቡ የቀብር ቦታን እና ማህበረሰባዊ የቀብር ስርዐትን እንዳያገኙ ማድረግን ይጨምራል። በጡረታ የተገለሉ ዜጎች የጡረታ አገልግሎታቸዉ እንዳያገኙ ተከልክለዋል፣ ስራ ያላቸዉም ከስራቸው እንዲባረሩ ታውጆባቸው ከስራም እየተባረሩ ይገኛሉ ።

ምንም እንኳ የገዢው ስርዓት የራሱን ጥቅም ለማስከበር ሲል ግልፅ የሆነ ከበባ ባያደርግም፣ አሁን እየተወሰደ ያለው እርምጃ የማህበረሰቡን ህልውና ጥያቄ ዉስጥ በማስገባት ተጽዕኖው ከሙሉ ከበባ የተናነሰ አይሆንም።

የኦነግ-ኦነሰ ከፍተኛ አዛዥ

ሚያዚያ 27፣ 2024

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading