• Sun. May 19th, 2024

በምዕራብ ወለጋ ዞን በመና ሲቡ ወረዳ ውስጥ ግድያና ዘረፋ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በፋሺስቱ የብልፅግና ቡድን በሰፊው እየተካሄደ ነው

May 5, 2024

ግንቦት 3/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ህብረቱሰቡን መግደል ጀግንነት የሚመስላቸው የብልፅግናው ጦር ቡድኖች በሄዱበት ቦታ ሁሉ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን ንጹሃን ሰዎችን “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መልዕክተኛ ናችሁ” በማለት መግደልን አጠናክረው ቀጥለዋል።

በዚህም መሰረት በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ መና ሲቡ ወረዳ፣ ኮኮራ ጉራቲ ቀበሌ ውስጥ መጋቢት 30፣ 2024 ኦቦ ጉተታ ባሪዎ የ4 ልጆች አባት እና ዋቅጂራ የተባሉትን በጥይት በመደብደብ ገድለው መጣላቸው ተሰምቷል።

በሌላ ዜና ደግሞ በኗሪዎች ላይ የንብረት ዘረፋ መፈጸሙን ሲነገር የዚህም ድርጊት ሰለባ የሆኑት፦

  1. ኦቦ ሀፍቴ ለሚ 2 ኩንታል ቡና፣ 7 ኩንታል ሚጥሚጣ እና 20 ኩንታል በቆሎ እና
  2. ኦቦ ኢታና ዋቅቶላ ሱቃቸው ውስጥ የሚገኘውን ንብረት ሙሉ በሙሉ ዘርፈዋቸዋል።

በተጨማሪም፦

  1. ከኦቦ ፊቃዱ ሀብቴ 16 ኩንታል ቡና
  2. ከኦቦ ፍቃዱ ሀብቴ እናት 4 ኩንታል ቡና እንደዘረፉና ወደ መንዲ ከተማ እንዳጓጓዙም ታውቋል።

የኦሮሞን ሕዝብ ቤት ንብረት በማውደም እና ንብረትን በመዝረፍ የኦኮኖሚ ጥገኛ ለማደረግ እና የኮሎኒያል ስርዓትን ለማስፋፋት የሚደርገው እኩይ ተግባር የማይሳካ መሆኑን ተገንዝበው በዚህ መስፈርት የተሰማሩትን ሁሉ አደብ ግዙ እንላለን።

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading