ግንቦት 12፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የብልጽግና ስርዓት በኋላ ቀር አስተሳሰብ ላይ የተገነባ የአንድ ብሄርን የበላይነት ለማስፈን እና ኦሮሙማን በማጥፋት ላይ ያነጣጠረ ነው። ይኸውም የኦሮሞ ልጆችን ከእስራት እና ከማሰቃየት ጎን ለጎን አንዳንዶቹን ከእስር ቤት አውጥቶ በመሰወር እና ደብዛቸውን በማጥፋት ጠላትነቱን እያረጋገጠ ይገኛል።
በዚሁ መሰረት በቄለም ወለጋ ዞን፣ ጋዎ ቄቤ ወረዳ፣ 01 ቀበሌ ውስጥ ይኖሩ የነበሩትን ኦቦ ኢብሳ ግርማን እና ቄሮ ቢቂላ አለሙ የተባሉ ሰዎችን ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሃሰት ውንጀላ ባለፉት ሶስት ወራት በቄቤ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ታስረው የነበሩ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከእስር ቤት አውጥተው ወዴት እንደወሰዱዋቸው እንዳልታወቀ የአካባቢው ነዋሪ ለአቢኦ ተናግረዋል።
ቄሮ ቢቂላ አለሙ ወንድሙ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባል በመሆኑ ብቻ ያለጥፋቱ ተወንጅሎ ታስሮ መቆየቱን እና የጤንነቱ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።
ኦቦ ኢብሳ ግርማ የአንድ ልጅ አባት ሲሆን ለኦነሰ ከከተማ ወደ ገጠር አንዳንድ አቅርቦቶችን ታመላልሳለህ እንዲሁም ትሰልላለህ ብለው እንደወነጀሉትም የእካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
