ግንቦት 15፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የብልፅግና ስረዓት በጠመንጃ አፈሙዝ በማስፈራራት የኦሮሞን ሕዝብ እንደ ባሪያ ለመግዛት እንዲያመቸው መግደል፣ ማሰር፣ ማሰቃየት እና መዝረፍ የዕለት ስራው ማድረግ ከጀመረ ስድስት አመት ሆኖታል።
በዚሁ መሰረት በቡኖ በደሌ ዞን፣ በጨዋቃ እና በቦኮ ወረዳዎች ውስጥ የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር የኦሮሞ ገበሬዎችንና በንግድ ዘርፍ እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩትን በመዝረፍ፣ በማሰር እና በመግደል ላይ ይገኛል። በዚሁ መሰረት ከ250 ኩንታል እህል በላይ ሲዘርፍ፣ ይህም ዝርፊያ ሕብረተሰቡን በድህነት ማቅ ውስጥ ከትቶ እና ተመፅዋች አድርጎ ለመግዛት ካቀደው ተንኮሎች አንዱ መሆኑን የአካባቢው ሕዝብ መረዳቱን ምንጮቻችን ነግረውናል።
ጨዋቃ ወረዳ
ሚያዚያ 1፣ 2024 በቡኖ በደሌ ዞን፣ ጨዋቃ ወረዳ ኦቦ አሊዪ አህመድ ሀሰን ከተባሉት 250 ኩንታል ‘ቦቤ’ ማሽላ በመኪና ጭነው ከጨዋቃ ከተማ ወደ አርጆ ጉደቱ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ መንገድ ላይ የፋሺስት አብይ ብልፅግና ሰራዊቶች አስቁመዋቸው እህሉን ምንም ሳያስቀሩላቸው መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
ኦቦ አሊዪ ለዚህ ዘረፋ የተጋለጡት በፓለቲካ ዉስጥ ተሳትፎ ኖሮዋቸው ሳይሆን ምንም ቅቡልነት የሌለው ምክንያት በመደርደር ይኸውም፥ “አመለካከትህ፣ የኦሮሞ ነፃነት አመለካከት ነው።” በማለት የሃሰት ውንጀላ የፋሺስቱ የብልፅግና ቡድን እቅርቦባቸው እንደሆነም ታውቆዋል። ይህንን ድርጊት በጠራራ ፀሐይ እየፈፀሙ ያሉበት ቁልፍ ምክንያታቸው ግን በአሁኑ ወቅት የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን ከባድና የማይወጣው የኢኮኖሚ ችግር ዉስጥ ስላለና ችግሩን ለመወጣት የሚተገብረው የግፍ ሴራ ነው በማለት የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ አክለው ገልጸዋል።
የኦሮሞን ሕዝብ ህልውና ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳው ፋሺስቱ የብልፅግና ቡድን በጨዋቃ ወረዳ፣ በዳበና ቀበሌ ውስጥ ሚያዚያ 17፣ 2024 ሰባት ኦሮሞዎችን ኮኦነሰ ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት በሃሰት ዉንጅላ እንዳሰሩዋቸው እና እያሰቃዩዋቸው መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀውናል። ከእነዚህ እስረኞች ውስጥ ሶስቱ ቃሬዎች መሆናቸው ታውቋል።
ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል ስማቸውን ያገኘነው፦ ቃሬ ሳዲያ፤ ኦቦ ኢብሮ ሙሳ እና ኦቦ አማዲን ሲሆኑ፣ ከኦቦ አማዲን 15,000ሺ ብር እንደዘረፋ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
መኮ ወረዳ
ከግድያ ዜና ጋር በተያያዘ ደግሞ በመኮ ወረዳ፣ ሻርኮ ቀበሌ፣ ልዩ ቦታው 7ኛ በተባለው አካባቢ የፋሺስቱ ብልፅግና ሰራዊት የሐገር ሽማግሌውን ኦቦ አሊሾ አብደላን (አባ ሙስጠፋ) ሚያዚያ 23፣ 2024 ጥይት እንደ ዝናብ አርከፍክፈው ገድለው፣ ጥለዋቸው መሄዳቸው ታውቋል።
ኦቦ አሊሾ የ60 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ በአካባቢያቸው ሰዎችን የሚያስታርቁ፣ የሀገር ሽማግሌ፤ ባሉበት ማህበረሰብ ዘንድም ትልቅ ክብር እና ተወዳጅነት ያላቸው ነበሩ። በፋሺስት አብይ የሰለጠኑት ገዳይ እና ዘራፊ ጦር ቡድን እኚህን አረጋዊ መግደል ሳያረካቸው ቀርቶ ንብረታቸውን በሙሉ ዘርፈው፣ አንድ በሬም አርደው እንደበሉም ምንጮቻችን ገልፀውልናል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”
