• Fri. May 15th, 2026

የአጭበርባሪ ሃሳዊ መሲሃንና የዕብሪተኞች የማይገባቸዉን የይገባናል አደንቋሪ ጩኸት

May 21, 2024

በኤሌሞ ቂልጡ

እስቲ አስቡት፣ የናዚ ደጋፊዎች በስልጣን ላይ ለመቆየት ብቻ ሲሉ በተባበሩት ኃይሎች መስዋዕትነት የተገኘዉን ድል እነሱ ያስመዘገቡት ድል በማስመሰል ከፍተኛ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ከፍተዉ በምስጋና ይገባናል ጥያቄ ቢያደነቁሩን፦ ትረካቸዉም በነፃ መውጣት አስፈላጊነት ላይ የሚያጠነጥን ቢሆንና፣ ነፃ የመዉጣትና ድሉንም ለመጎናፀፍ የተቻለው በእነርሱ ትጋት እንደሆነ ብዙሃኑን ለማሳመን ያላሰለሰ ሙከራ ቢያደርጉ። እንድህ ዓይነቱ ጥረት እውነትን ለማዛባት የሚደረግ ፕሮፖጋንዳ ሲሆን፣ የሚረዳውም የውድቀታቸውን ጥልቀትና፣ ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ያለምንም ሃፍረት የሚሄዱትን ርቀት ፍንትው አርጎ የሚያሳየን ድርጊት መሆኑን ነዉ።

የሚሰቀጥጠው ድርጊት ግን ሽንፈታቸው እየታየም እንኳ ምንም ዓይነት ጸጸት አለማሳየታቸው ሲሆን፤ ይባስ ብለው በገሃድ የሚታየው እውነታ ግን ስልጣንን ሙጥኝ ብለዉ በመያዝ ያለምንም ርህራሄ ንፁሃንን በገፍ ማረዳቸው፣ ነዋሪዎች ቤታቸው ዉስጥ መኖራቸው እየታወቀ የገጠር መንደሮችን በእሳት ማጋየታቸው እና ንብረታቸውን ማውደማቸው ሲሆን ላወደሙት ንብረት፣ በእሳተ ነበልባል ተቃጥለው ለሞቱት ነዋሪዎችና በጠቅላላው ለፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በሙሉ በቀጥታ ተጠያቂ መሆናቸው ነው።ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ለፈፀሙት አሰቃቂ ወንጀል ተጠያቂ ላለመሆንና ስልጣን ለመጨበጥ በቅጽበት አቋማቸውን ሲቀያይሩ መታየታቸው ነው። የአሁኑ የአቋም ትርክታቸዉ ከቀድሞው የጅምላ ግድያ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ድርጊቶቻቸው ጋር ሲተያይ ተፃራሪ ነው። እውነታን ለማዛባት ያለምንም ሃፍረት ‘የነጻነት ታጋዮች ነን’ የሚለው ድፍረት የተሞላበት ንግግራቸዉ አልቦ ስነ ምግባር መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ከላይ የተጠቀሱት ክሁነቶች የሚጠቅሙት ግለሰቦቹ ምንም የተቀዳጁት ስኬትም ሆነ ለመተግበርያ እውቀት ሳይኖራቸው በሃሰት ትርክት እውቅና ለማግኘት የሚጥሩ መሆናቸው ነው። ዛሬ ፖለቲካ በማጠንጠን በሚመራበት ዘመን ውስጥ ፕሮፓጋንዳው ከእውነት ርቆ ”አማራጭ እውነታዎች” የሚለው መርሆ በሚያሳስብ ደረጃ እየተስፋፋ ሲሆን፣ ፖለቲከኞችም ስለ ስኬታቸው ሆነ ስለችሎታቸው የተጋነነ ወይም ከእውነት የራቀ መረጃ መናገርን ልምድ አድርገዉታል።

በራስ መተማመን ብዙ ግዜ ከታማኝነት እኩል ይታያል፣ ይህም ከብዙ ጫና በኋላ ፕሮፓጋንዳን እንደ እውነት ይቀበላል፣ ወደ አደገኛ አዝማሚያም ያመራል። ይህም ባህርይ የሚመጣው ራስን ካማከለ አስተሳሰብ፣ በራስ ያለመተማመን፣ ከሌላ ሰው ማረጋገጫ መጠበቅ ሲሆን ውጤቱም አደገኛ፣ እምነትና ተዓማኒነትን የሚሸረሽር ነው።

እንደዚህ ዓይነቱ የሥነ፡ምግባር ጉድለት ብቻ ሳይሆን እጅግ በጣም አደገኛም ነዉ። እነዚህ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ረድፋቸውን በሁለትዮሽ (ቢፖላር) የመገለጫ መንገዶች ለመጓዝ መምረጣቸው ዋና አጀንዳቸውን ያበላሸዋል፥ “በማንኛውም መንገድ እና ወጪ ስልጣንን መቆናጠጥ።” የእነሱ ፖለቲካ ስልት የተገነባው ከሰፊው ሕዝብ ደህንነት ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም በማስቀደም፣ ህዝቡን በማጭበርበር፣ አመፅና መከራ እንዲፈራረቅበት እና ስቃዩም እንዲቀጥል በማድረግ ነው።

እስከ ዛሬ የትም ቦታ ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን አገላለፅ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መረጃ በቅርቡ ጋዜጠኞች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች በተገኙበት በነቀምቴ ከተማ ስታድዮም በአረመኔዎቹ ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና ፕሬዝደንት ሽመልስ አብዲሳ ካደረጉት ንግግር በላይ የለም።

በድፍረትና በጋለ ስሜትም እራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን በተፃራሪ መስመር መቆማቸውንም ወደ ጎን ትተው ለ“ሕዝባቸው” የነፃነት ታጋይም ነን ብለው ብቅ ብለዋል። አምባገነኖች፣ ጨቋኞች፣ ገዳዮች፣ አፋኞች፣ የሰብዓዊ መብት ረጋጮች እና በትግል እየተደገፈ የመጣውን የነፃነት ነበልባል ለማፈን ቢሞክሩም ያልተሳካላቸው መሆኑን በመዘንጋት ዛሬ ደርሰው የነፃነት ዘብ ነን ብለው ያውጃሉ። እነዚህ ደፋሮች ለመሆኑ ለይገባኛል መልዕክታቸው ሃፍረት ይሰማቸው ይሆን?

በኦሮሞ ጥበብ መስክ አንድ ምሳሌያዊ አነጋገር አለ፥ “Kan na afuufan, na liqimsuufi, jette marqaan.” በሚንበለበለው ሙቀት ዉስጥ በመንተክተክ ላይ ያለው ገንፎ ይህንን ድምፅ ያሰማል፥ “ገንፎ ሁፉፉፉ የሚሉሽ ሊዉጡሽ ነዉ!”

ቅድመ ማስጠንቀቂያውና በማር የተለወሰው ንግግራቸው የኦሮሞ ነፃነትን የሚያወድሱ በሚመስሉ ቃላቶች የታጀሉ ስለሆነ በጥንቃቄ መመልከት ተገቢ ነው። የአራዊቶቹ ንግግሮች እና አላማቸው የሚፃረሩ ስለሆነ ሕዝባችን ንቁና ጠንቃቃ እንዲሆን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያሳስባል።

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading