ግንቦት 31፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ANO)
ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የፋሺስት ብልፅግና ጦር ኃይል የ40 ቀናት የዘመቻ ዕቅድ አውጥቶ በኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ የተሰማራውን ለማኮላሸት ተከታታይ እርምጃ ሲወስድ የነበረ ሲሆን፣ ከግንቦት 28፣ 2024 ጀምሮ ደግሞ የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻን ተመርኩዞ በተቀናጀ መልኩ እየወሰደ ባለው የማጥቃት እርምጃ አኩሪ ድል እያስመዘገበ ይገኛል።
ግንቦት 29፣ 2024 “የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ”
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምስራቅ ወለጋ፣ በሳሲጋ ወረዳ፣ በጂማቴ ከተማ እና በጉቶ ጊዳ ወረዳ፣ አዳሚ ቀበሌ ውስጥ ከባባድ እርምጃ በጠላት ኃይል ላይ እንደወሰደ አቢኦ በጦር አዛዦች በኩል አረጋግጦዋል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በደቡብ ዞን ባደረገው የተቀናጀ ጦርነት አኩሪ ድል አግኝቷል። በዚሁም ሁኔታ በቦረና ዞን፣ በሚዮ ወረዳ፣ በዱከሌ ቀበሌ የጠላት ኃይል ለረዥም ጊዜ ሰፍሮበት የነበረ ካምፕ በመግባት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጠንካራ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል። በዚህ ጦርነት ላይ ዞኑ ካለው 13 ወረዳወች ውስጥ ከ10 ወረዳዎች ላይ የኢምፓየሪቷ የመከላከያ ሰራዊት በመገኘት የተሳተፉ ሲሆን፦
- 41 ወታደሮች በሙት፣
- 52 መትረፍ በማይችል ቁስለኛ ተቀጥተው፣ የተቀሩት ለግዜው ከካምፑ ውስጥ ወጥተው ወይም ተፈናቅለው ለየብቻ ተበታትነዋል።
ግንቦት 27 እና 28፣ 2024
በመካከለኛው ዞን በተለያዩ ወረዳዎች እና እንዲሁም ለፊንፊኔ ቅርብ በሆኑ ከተሞች ውስጥ ጠንክሮ ቀጥሎ ነበር።
ግንቦት 21፣ 2024
በምዕራብ ሸገር ዞን፣ በአቡነ ግንደበረት ወረዳ፣ ካቢ ቀበሌ ውስጥ በወሰደው እርምጃ፦
- 40 የብልፅግና ኮማንዶ እና 8 ሚሊሻዎችን በሙት በመቅጣት ሌሎቹን ደግሞ አቁስሎ መሸኘቱ ታውቋል።
በመካከለኛው ሸገር ሰሜን ዞን፣ በደገም ወረዳ፣ በያያ ሀሮ ቀበሌ እና በምዕራብ ሸገር ዞን፣ በሜታ ወልቂጤ ወረዳ፣ በሰንዳፋ ቦነያ ቀበሌ፣ ቆጫ በሚባል ቦታ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ጠላትን አርግፏል።
በደገም ወረዳ ጦርነት ከፋሽስት የብልፅግና ጦር ላይ፦
- 9 ሲሞቱ፣
- 3 ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል።
በሜታ ወልቂጤ ውስጥም እንዲሁ በሞት እና በቁስለኞች ተቀጥተዋል። ከተገደሉትም መሃከል የጦር አዛዥ እንደነበረ ታውቋል።
በአቡና ግንደበረት ወረዳ በቢቴ ከተማ ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የጠላት ካምፕ ባሉበት በመሄድ በፈፀመው ጥቃት ከካምፑ አባርሮ አስወጥቷቸዋል። በዚህ ጦርነት ውስጥ የተገኘው ድልም፦
- 27 የጠላት ወታደር በሞት ሲቀጣ፣ ከእነዚህ ከተገደሉት ሰራዊቶች ውስጥ የአቡና ግንደበረት ወረዳ ምክትል የጦር ኃይል አዛዥ ኮሎኔል ዓለሙም ይገኝበታል፣
- 6 ሚሊሻዎች ተገድለዋል፣
- 10 ወታደሮችም ቆስለዋል።
በመሳሪያ በኩል፦
16 AKM ከትጥቅ ጋር፣ ጥይቶች እና ልብስ ከጠላት ጀርባ ላይ ሲፈቱ፣ አንድ ፖትሮል የጦር መኪናም ተቃጥሎ ወድሟል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚወስደው እርምጃ እስከ ነፃነት እና ኦሮሚያ ሉዓላዊ ሀገርነትዋን እስከምትጎናፀፍ ይቀጥላል!
