ግንቦት 30፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ግንቦት 9፣ 2024 በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የኑዌር ብሔረሰብ ተማሪዎች ባስነሱት ረብሻ ዘጠኝ የኦሮሞ ተማሪዎች መጎዳታቸው ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። እስከ አሁን በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ከባድ የአካል ጉዳት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ መድረሱን አቢኦ ከምንጮቹ አረጋግጦዋል።
በኑዌር አና በአኙዋክ ብሔረሰቦች መካከል በተለያየ ጊዜ በክልሉ ውስጥ በሚፈጠር ግጭት በኦሮሞና ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ላይ ከቀዬአቸው መፈናቀል እና በጉዞ ላይ እያሉ የመገደል አደጋ እንደሚደርስባቸው ይታወቃል።
ፋሺስት አብይ አህመድ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል የማይፈነቅለው ድንጋይና የማይጭረው ፀብ የለም። በብሔር ብሔረሰቦች መካከል የጎንዮሽ ማለትም በኦሮሞ ሕዝብና በሌሎች ጭቁን ሕዝቦች መካከል ፀብ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉት በእርሱ የተመለመሉ ካድሬዎች እንደሆኑ በግልፅ እየታየ ነው። ስለዚህ ጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች የዚህን የፋሺስት ግለሰብ ድርጊት በጥሞና እንድትከታተሉት እናሳስባለን።
