• Sun. Mar 15th, 2026

ፋሺስቱ የብልፅግና ቡድን በአርሲ ዞኖች ኦሮሞዎችን ይገድላል፣ ይዘርፋል፣ ለጦር ሜዳም ጥይት ማብረጃነትም ልጅ፣ አዋቂና ሽማግሌ ሳይል በግዳጅ እያፈሰ ይገኛል፤ ይህ ሁሉ እስከመቼ?

Jun 3, 2024

ሰኔ 3፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በምሥራቅና ምዕራብ አርሲ ዞኖች የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር ቡድን ሰላማዊውን ሕዝብ ከመዝረፍ፣ ከማሰር፣ ከማሰቃየት እና ከመግደልም ጎን ለጎን “አብይን በስልጣን ላይ ለማቆየት የኦሮሞን ሕዝብ ቁጥር መቀነስ” በሚል አጀንዳ የደሃ ልጆችን በግዳጅ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማጋዙን ቀጥሎበታል። ይህም የወታደራዊ ኃይል ስልጠና የኦሮሞን ሕዝብ በተለያየ መንገድ ለማጥፋት የተቀነባበረ ስልት ነው።

ህፃናትን ከአስራ ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ህፃናትን እና በእድሜ የገፉ አዛውንትን ሳይቀር አስገድዶ በማፈስ በመኪና በመጫን ቤተሰቦቻቸውን ለመከራ እና ሀዘን እንደዳረጋቸው በሁለቱ የአርሲ ዘኖች የሚኖሩ ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።

ግንቦት 27፣ 2024 በቁጥር ከ30 መኪናዎች በላይ ለሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር እና ለአርሲ ነገሌ በማቅረብ የታፈሱትን ህፃናትን አዛውንቶች ወደ ተለያየ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፕ እንደላኳቸውም አቢኦ ከምንጮቹ አግኝቷል። እንደ ወላጅ “ጨቅላ ልጁን ወደ ጦር ሜዳ አትውሰድ” ማለት ህይወት ስለሚያስከፍል ልጆቻቸውን “አምላክ ይጠብቃችሁ” እያሉ መሸኘታቸውን ወላጆችና ቤተ ዘመዶች ለአቢኦ አክለው ገልፀዋል።

እንዲሁም በምሥራቅ አርሲ፣ ሽርካ ወረዳ፣ ዋጂ ራጳሳ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩት እና የአራት ልጆች አባት የሆኑትን ኦቦ ሙሳ ከድር የተባሉትን ሚያዚያ 24፣ 2024 እቤታቸው ድረስ በመሄድ 30 ሺ ብር ከዘረፍዋቸው በኋላ እዚያው ገድለዋቸው እንደሄዱ የዓይን እማኞች ለአቢኦ ገልፀዋል።  

#የሽኒጋ_ቃልኪዳን_ዘመቻ

ኦቦ ሙሳ ከድር ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ የሆኑና በአከባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ተወዳጅና የተከበሩም እንደነበሩ ምንጮቻችን አክለው ነግረውናል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚወስደው እርምጃ እስከ ነፃነት እና ኦሮሚያ ሉዓላዊ ሐገርነትዋን እስከምትጎናፀፍ ይቀጥላል!

ድል ለኦሮሞ ሕዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading