• Wed. Nov 25th, 2026

ጀግናው እና የኦሮሞ ሕዝብ መከታው የደቡብ ኦሮሚያ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ዕዝ በቦረና ዞን፣ በዲሎና በዲሬ ወረዳዎች ውስጥ ባደረገው የደፈጣ ጥቃት በጠላት ላይ ትልቅ ድልን ተጎናፅፏል 

Jun 11, 2024

ግንቦት 24፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በዲሎ ወረዳ፣ ሆቦቅ ቀበሌ

ሚያዚያ 5፣ 2024 በበዲሎ ወረዳ፣ ሆቦቅ ቀበሌ የአካባቢውን ሕዝብ ሲያሰቃይ የነበረ የፋሺስቱ ብልፅግና ሰራዊት በአንድ መኪና ሙሉ ተጭነው እየተጓዙ ሳለ የኦሮሞ ሕዝብ አለኝታው ኦነሰ፣ ጭብራ በዳ ደራር፣ ባደረገው የደፈጣ ማጥቃት እርምጃ ሙትና ቁስለኛ ከማድረጉም በላይ መኪናውንም ማግደዉታል።

በመሳሪያ በኩልም አንድ PKM እና 15 AKM ከጠላት ጀርባ በመፍታት ለነፃነት ትግሉ ገቢ አድርገዋል።

ዲሬ ወረዳ፣ መገዶ ቀበሌ

ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሚያዚያ 3፣ 2024 በኮሪ መንደር፣ ውስጥ ለስድስት ሰዓት (ከቀትር 6 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት) በተካሄደው ጦርነት 6ቱን ገድሎ 12 ከባድ ቁስለኛ ሲያደርግ የተቀሩት ደግሞ በተለያይ አቅጣጫ እግሬ አውጪኝ ብለው ፈርጥጠዋል።   

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ማለት እኛ ነን!

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ እና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply