• Mon. May 4th, 2026

የኮሎኔል አብይ አህመድን ዙፋን ለመጠበቅ ሰልጥነው ወደ ምሥራቅ አርሲ ዞን በሲርካና ጃጁ ወረዳዎች ከተሰማሩት ሁለት የኦሮሞ ልጆች የኢምፓየርዋን ሰራዊት በመካድ ለኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እጃቸውን ሰጡ

Jun 11, 2024

ግንቦት 5፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ለፋሺስቱ የብልጽግና ስርዓት በማገልገል ላይ ያሉ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች ስርዓቱን በመክዳት ወደ ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እየተቀላቀሉ ነው። በዚህ መሰረት ሚያዚያ 21፣ 2024 በምሥራቅ አርሲ ሽርካና ጃጁ ወረዳዎች ሁለት የስርኣቱ የሰራዊት አባላት ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው በአከባቢው የሚንቀሳቀሰውን የኦነሰ ተቀላቅለዋል። እነርሱም፦

  1. እብድ ገላና በሲርካ ወረዳ፣ ጠሬታ ከተማ 1 AKM፣ 2 F1 እና 200 ጥይቶች
  2. ሁለተኛው ደግሞ ከጃጁ ወረዳ፣ ጅማቴ ከተማ ሲሆን 1 AKM፣ 8 ጉምቢ፣ 3 F1 እና 400 ጥይቶች ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ገቢ አድርገዋል። 

የሕዝባቸውን ትግል ወደ ሚያካሂደው የኦነሰ የተቀላቀሉት ወታደሮች ብዙ ቁጥር ያላቸው የኦሮሞ ልጆች የመብት ጥያቄ በሚያነሱበት ወቅት በኦሮሞነታቸው ብቻ ከኦነሰ ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት እና የሃስት ወንጀል በማቀነባበር እስራትና ግዲያ እንደተፈፀመባቸውም ምስክርነት ሰጥተዋል።  

በገዳዩ የብልፅግና ስርዓት ውስጥ የቀሩት ሌሎች የሰራዊቱ አባላት የያዙትን ትጥቅ በመያዝ ወደ ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እንዲመጡም ጥሪ አስተላልፈዋል።

#የሽኒጋ_ቃልኪዳን_ዘመቻ

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading