ሰኔ 13፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጠንካራ ነፃነትን የመጎናጸፍ አላማ እና የሞራል ጽናት ስላለው የፋሽስት አቢይ አህመድ ጦር ቡድንን የሚይዘውና የሚጨብጠውን አሳጥቶት ደም እንደላሰ ዉሻ የፍልሚያ ሜዳውን በመተው በከተማና በገጠር ያሉ ንፁሃን ኦሮሞዎችን በማሰቃየት ላይም ይገኛል። ከዚህ በታች የተዘረዘረው የድል እርከን የኦሮሞ ጠላት ኃይል ብዙ እድሜም እንደሌለው ያመላክታል።
የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻና ድሎቹ
ከግንቦት 28፣ 2024 ጀምሮ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው “የሽኒጋ ቃል-ኪዳን” ዘመቻ ተጠናክሮ እየሄደ ይገኛል። በዚህ ዘመቻ አስተማማኝ ድሎች በብልፅግናው መንግሥት ላይ የተቀዳጀ መሆኑን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለአቢኦ አስታውቋል።
ሰኔ 3፣ 2024
በምዕራብ ኦሮሚያም፣ አንበሶቹ የምዕራብ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የታወጀውን የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ ጦርነት በማስቀጠል በምዕራብ ወለጋ በዩብዶ ወረዳ፣ የሞ በሚባል ቦታ በወሰደው የማጥቃት እርምጃ ስምንት የስረዓቱን ወታደሮች ሲገድል፣ 30 በቁስለኛነት በመቅጣት ከእነዚህም ውስጥ ሶስቱ ቁስለኞች የገንጂ ጤና ጣቢያ ከተወሰዱ በኃላ መሞታቸውን ከብልፅግና ጦር ውስጣዊ መረጃ አቀባያችን አብራርቷል።
በዚህ ጦርነት፦
- አምስት AKM ጠመንጃ፣
- 500 የብሬን ጥይት፣
- 400 የክላሽ ጥይት፣
- 18 የተዘጋጀ ሬሽን እና
- አንድ ባለ 200 የብሬን ጆሮሮ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከጠላት ጀርባ በመፈታት ለኦሮሞ የነፃነት ትግል ገቢ አድርጎዋል።
በዚሁ ዕለት በተመሳሳይ ሁኔታ በደቡብ ኦሮሚያም ለጠላት እረፍት የማይሰጡት አነሮቹ የደቡብ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት፣ ጠዋት ማለዳ ከ11:30 ጀምሮ በቦረና ዞን፣ በጎመሌ ወረዳ፣ በDhaካ በሩ ቀበሌ፣ ፉላ ሂዶ በሚባል ቦታ ካምፕ ሰርቶ በነበረው የብልፅግና ጦር ላይ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ ብዙዎቹን በሞት እና በቁስለኛነት ቀጥቷል።
ሰኔ 2፣ 2024
በማዕክላዊ ኦሮሚያ ዞን በተወሰደው እርምጃ በርካታ ቁጥር ያላቸው የብልፅግና ሰራዊትን ደመሰሶዋል። ከተደመሰሱት ውስጥም ሁለት ወታደራዊ የበላይ አመራሮች እንደሚገኙበትም ተረጋግጦዋል።
የህዝብ ጋሻ የሆነው የሀርሰዴ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዞን የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻን በመመርኮዝ በጠላት ላይ የጀመረውን የማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ በመቀጠሉ ወራሪው የፋሺስት ብልፅግና ጦር ከምስራቅ ሸገር ዞን ከዱግዳ ወረዳ ወደ ሀፋ ቀመሌ ቀበሌ ካፌ በሚባል ቦታ ላይ መስፈሩን ተገንዝቦ አይበገሬው የኦነሰ በድንገት ደፈጣ በማድረግ ረዘም ላለ ሰዓት ጦርነት ተካሂዶዋል። በዚህም ጦርነት 51 በሞት ሲቀጣ 30 ደግሞ ማገገም በማይቻል ቁስል በመቅጣት ጠላትን ሸኝቷል። የሰላማዊ ዜጎችን ቤቶች ለማቃጠል ከጦሩ ጋር አብረው ሲሄዱ የነበሩትን አራት ሰላዮችን ደግሞ ማርኳል።
በዚህም ጦርነት የሚከተሉትን የጦር መሳሪያዎች ከጠላት ጀርባ በመፍታት፦
- 15 AKM ጠመንጃ፣
- 15 ሙሉ ትጥቆችን እና
- በቁጥር ብዙ ጥይቶችን የኦነሰ ለነፃነት ትግሉ አበርክቷል።
ግንቦት 29፣ 2024
በምሥራቅ ዞን በምዕራብ ሐረርጌ፣ ጉሚ ቦርደዴ ወረዳ የኢትዮ-ጂቡቲን መንገድ በመቆጣጠር ረዘም ላለ ሰዓት በወሰደው እርምጃ በብልፅግናው መንግሥት ወታደሮች ላይ ወታደራዊ ኪሳራ አድርሶባቸዋል። የኦነሰ ኦፕሬሽኑን በሶስት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ከፋፍሎ በወሰደው ከባድ እርምጃ መሰረት መንገዱን ሲጠብቁ የነበሩትን የጠላት ሃይል ከቦታው በመንቀል ድል አስመዝግቧል። የብልፅግናው መንግሥትም በዚህ ጥቃት በመደናገጥ አዳዲስ ወታደሮችን ከኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ወደ ቦታው እያጓጓዘ መሆኑ ታውቋል።
ምክትል ኤታማጆር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ “የኦነሰ የረጅም ግዜ እቅድ እና የጋራ አዛዥ የለውም” በማለት የመንግሥት ወታደሮችን ለመቀስቀስ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። የኦነሰ በምዕራብ፣ ምሥራቅ፣ በደቡብ፣ በሰሜን እና በመሃከል ኦሮሚያ ያሉት ሁሉ በአንድ ዕዝ ስር ሆነው አንድ መርሆንም አንግበው የ “ኢርቡ ሽኒጋ” ዘመቻን ከግቡ ለማድረስ ጠላትን ወደማያገግምበት ማቅ ውስጥ በመክተት በርካታ የጦር መሣሪያዎችንም እያስፈታ መሄኑን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አስታውቋል።
የኦነሰ የቅድመ “የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ” ዝግጅት ድሎቹ
ግንቦት 24፣ 2024
በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ በቡሌ ሆራ ወረዳ፣ በበዳ መጋዳ ደን ዉስጥ ሀሮ ደነባ በሚባል ስፍራ፤ ጀግናው የኦሮሞ ህዝብ ተስፋ የሆነው የኦነሰ የማፍያው ብልፅግና ጦርን በበዳ መጋዳ ደን ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን እናጠፋለን በሚል ስም ደኑን እየመነጥሩ ሳሉ አድፍጦ ከ8:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት ከባድ እርምጃ ወስዶዋል። እነዚህን ከተለያየ ቦታ ለእኩይ ተግባር የተሰባሰቡትን የጠላት ኃይል የኦነሰ ከ40 በላይ እንዳያንሰራሩም ሲቀጠፍ ከ30 በላይ የሆኑትን ደግሞ በማይሽር ቁስል ተሸኝተዋል።
በዚሁ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ውስጥ በቦረና ዞን፣ በአራሮ ወረዳ፣ በሂርማዬ ቀበሌ የመደ አልቡዳ ጭብራ እና የጎሮ ዱግዳ ጭብራ አንድ ላይ በመሆን ለረዥም ጊዜ የኦሮሞ ህዝብ ላይ ድብደባ እና ማሰቃየት ሲፈፅም የቆየ የብልፅግና ጦር ላይ በጠራራ ፀሀይ በወሰደው እርምጃ እንደ ቅጠል አርግፎአቸው ብዙዎቹን በሙት እና በቁስለኛ በመቅጣት የቀሩትም ወደ ተለያየ አቅጣጫ እንዲበታተኑ አድርጎዋቸዋል። በዚህም ፍልሚያ የወታደር ዩኒፎርም እና በሺህ የሚቆጠሩ ጥይቶችን ወደ ነፃነት ትግሉ ገቢ ሆኖዋል።
ግንቦት 12፣ 2024
በምዕራብ አርሲ ዞን፣ አዳባ ወረዳ ውስጥ ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጠላት “የኦነሰን አሰሳ እናደርጋለን” በሚል ተሰማርተው ሰላማዊ ሰዎችን እያሰቃዩ ባሉበት ወቅት ነብሩ የኦነሰ እነርሱኑ በመክበብ አሳራቸውን ካሳየ በኋላ ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉም አድርጓቸዋል።
የደቡብ ምሥራቆቹ አንበሶች የመደ ወላቡ ብርጌድ በምዕራብ አርሲ ዞን፣ አዳባ ወረዳ ውስጥ የብልፅግና ሰራዊት “የኦነሠን አሰሳ አደርጋለው” በሚል ሰላማዊውን ህዝብ ያለምንም ጥፋት እየገደሉ፣ እያሰሩ፣ ቀዬአቸውን እያወደሙ እና ንብረታቸውን እየዘረፉ የነበሩትን በከበባ በወሰደው እርምጃ 10 የአብይ አህመድ ወታደሮች ወዲያው ሲገደሉ፣ 7ቱን ደግሞ በማቁሰል እና የተረፉትም ከአካባቢው በማባረር አኩሪ ድል አስመዝግቧል።
በተያያዘ ዜና በዚሁ ዞን እና ቀን የጃል ነdhi ገመዳ ብርጌድ በጠላት ላይ እየወሰደው ያለው እርምጃ መቀጠሉን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ጠንካራ አቅዋም ያላቸው ጀግኖች በምሥራቅ አርሲ ዞን፣ ሙኔሳ ወረዳ፣ ቀርሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ግንቦት 11፣ 2024 ሌሊት ጠላትን ሲያምሱ ማደራቸው ታውቆዋል።
በቁጥር ብዛት የጠላት ሙትና ቁስለኛ መቆጠሩ በጠላት ካምፕ አካባቢ ድንጋጤ እንደ ፈጠረ ምንጫችን ነግሮናል።
እንዲሁም የብልፅግናው ተላላኪ ጦር ቡድን የሰፈሩበት ካምፕ ውስጥ በድንገት ዘው ብለው በመግባት ወዲያው 6ቱን ሲገድል 18ቱን አቁስለሎ በተጨማሪም 200 PKM ጥይቶችን እና የዝናብ ልብሶችን ማርኮ ለነፃነት ትግሉ ገቢ አድርጎዋል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ ጦርነት የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ድል ለኦሮሞ ህዝብ እና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Long Life O L F Uʻ