ሰኔ 18፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ትጥቅ ያልታጠቀ እና ዱላ እንኳ በእጁ የሌለውን ህዝብ በጦር ሜዳ በተሸነፉ ቁጥር ሲዝቱበት የሚውሉት የማፍያው ብልፅግና ሰራዊት በሁሉም ኦሮሚያ ዞኖች የጭካኔ ተግባራቸውን አስፋፍተው ቀጥለውበታል። የማፍያው ብልፅግና ስርዓት፣ ስርዓት ጠባቂዎች ምን ያህል ስብዕና የጎደለው ስልጠና እንደሚሰጣቸው ከግዜ ወደ ግዜ በሚተገብሩት ስራ ማወቅ ይቻላል። ሊያጓጉዙት ያልቻሉትን በኩንታል የተቀመጠ እህልንም በሳንጃ በሳስቶ እንዲፈስስ ማድረግንም ተክነዋል።
ሰሜን ኦሮሚያ፣ ወሎ ዞን
በሰሜን ኦሮሚያ ያለው የማህበራዊ ቀውስና ፀጥታ ሁኔታ የበለጠ አስከፊ እየሆነም ሄዶዋል። የፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና ጦር ቡድና እና እራሱ አደራጅቶዋቸው የነበረውና አትንኳቸው የሹም ዶሮዎቼ ናቸው በሚል መልኩ ሲያንቆለጳጵሳቸው የነበሩት የአማራ አሸባሪው ፋኖ ቡድንም ጋር እየተናበቡ የኦሮሞን ህዝብ በፈረቃ እያሰቃዩ መሆኑን በተለያየ ወረዳ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገሩ።
ግንቦት 29፣ 2024 በደጉጉሩ ወረዳ፣ መታሃራ ቀበሌ ውስጥ የተሰማራው የብልፅግና ታጣቂ ቡድን ህዝቡን በግድ መሰብሰባቸውንና ስብሰባውን የቀረ ሰው እስራትና የገንዘብ ቅጣት እንደሚደርስበትም ቀደም ብለው በማሳወቃቸው የቀበሌው ነዋሪዎች ጥሪውን ሳይወዱ በግድ በመቀበል ስብሰባው ላይ ተገኝተውም ነበር። ሆኖም ግን የሚከተሉትን ንፁሃን ገበሬዎችን፦
- ኦቦ ጉራቻ ተምሶ፣
- ኦቦ መሐመድ አህመድ እና
- ኦቦ መሐመድ ጂፊ የተባሉትን እዛው በስብሰባው ላይ “እናንተ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ደጋፊዎች ናችሁ!” በማለት እርሻቸውን አርሰው የሚኖሩና ምንም ዓይነት የፖለቲካ አስተዋፅኦ የሌላቸውን ክፉኛ በመደብደብ የአካል ጉዳትም እንዳደረሱባቸው የቀበሌው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
ከግንቦት 28፣ 2024 ጀምሮ በዳዋ ወረዳ ስር በሚገኙ በርካታ ቀበሌዎች ውስጥ የተሰማራው የብልፅግና ስርዓት ጦር ቡድን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ክፉኛ ድብደባና እስራት እየፈጸመ ይግኛል::በዚህም መሰረት፦
- አህመድ ኑሩ
- መሐመድ አባዩ እና
- አብዱ ኢብራሂምን ክፉኛ ከደበደቧቸው በኋላ ቦራ ከተማ አስተዳደር ውስጥ እንዳሰሩዋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልጸዋል።
ይህንንም እኩይ ድርጊት የፋሺስት አብይ አህመድ ጦር ቡድን የፈፀመው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ግንቦት 28፣ 2024 በወሰደው የማጥቃት እርምጃ በመደናገጥ ሲሆን፣ በአካባቢው በሚገኙ በሁሉም ቀበሌዎች ውስጥ ሰላማዊ ሰዎችን ማሰርና ማሰቃየቱንም ቀጥለውበታል።
ከዚህም በላይ በጂሌ Dhuሙጋ ወረዳ፣ ሂዳ ብሎ ቀበሌ ውስጥ ከግንቦት 28፣ 2024 ጀምሮ የስርዓቱ ጦር ቡድን በከፍተኛ ኃይል ወደ ህዝቡ ተሰማርተው የሚከተለውንም የሚያሸልም የግፍ ዘመቻ፥ “አንድ ሰው በሂዳ ብሎ ቀበሌ ውስጥ የሚኖር አንድ ግለሰብን ከገደለ 50ሺ ብር እና አንድ ጠመንጃ ይሸለማል!” በማወጅ ሚሊሻዎችን ከመመልመሉም ባሻገር የተመለመሉትም ሚሊሻዎች በቀበሌው ለአንድ ሳምንት በማስፈር ህዝቡን ሲያሰቃዩ ቆይተዋል።
የሂዳ ብሎ እና ያቱ ቀበሌ ውስጥ የሚኖረውም ህዝብ ህይወቱን ለማዳን ከቄዬው በመፈናቀል ጫካ ውስጥ በረሀብ፣ በፀሃይ ሐሩር እና በብርድ እየተሰቃየ ይገኛል። የስርዓቱ ሚሊሻዎችም እነዚህን ነፍስ አውጪኝ ብለው የሚሸሹትን በመከታተል ግንቦት 28፣ 2024 ተኩስ በመክፈት የህዝብ ንብረት ከመዝረፋቸውም በላይ ህፃናት፣ እናቶችን እና አዛውንቶችን እንደጨፈጨፉ ታውቋል።
እነዚሁ ሚሊሻዎች በአርጆ ቀበሌ ውስጥ ይኖር የነበረን የ18 ዓመቱን ቄሮ አደም አብደላን ይዘው ማሰራቸው ታውቋል።
ምዕራብ ሸገር ዞን
በባኮ ቲቤ ወረዳ፣ ወርዲ ሶምቦ ዲሳሳ ቀበሌ ውስጥ የብልፅግናው ጦር ካምፕ ውስጥ ከሚሰቃዩት በከፊል ስማቸውን አቢኦ ለማግኘት የቻለው፦
- ኦቦ ረታ ጭምዴሳ፣
- ኪፍሌ፣
- የኦቦ ደቻሳ ደረጀ ቤተሰቦች በሙሉ፣
- ኦቦ ገበየሁ ታፈሳ፣
- ኦቦ ገመቹ ናቸው።
በዚሁ ወረዳ ብዙ ሰዎች ከቄዬአቸው እና ከንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ ይህም የሆነው አንዳች ጥፋት ኖሮባቸው ሳይሆን በማንነታቸው (ኦሮሙማነት) ምክንያት ብቻ የመኖር ህልውናቸው አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱንም የቀበሌው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገሩ።
ምስራቅ ወለጋ ዞን
በዲጋ ወረዳ፣ ቡርቃ ጉዲና ቀበሌ ውስጥ ሰዎች ያለ አንዳች ጥፋት የታሰሩ እና ንብረታቸው የተዘረፈባቸው ሰዎች በቁጥር ብዙ ሲሆኑ፣ ከእነሱ ውስጥ አቢኦ ስማቸውን ያገኘው፦
- ኦቦ ፉፋ በdhaaሳ፣
- ኦቦ ኢሊያስ ከበዳ፣
- ኦቦ ኢዶሳ መረባ፣
- ኦቦ ጉደታ በንቲ እና
- ኦቦ ታረቃ መንኪራ ይባላሉ።
የብልፅግናው ጦር ቡድንም ከላይ የተጠቀሱትን ግለሰቦች በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ አስረው ከማሰቃየትም በላይ ቤታቸው ውስጥ በመግባት ዕቃዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ከመሰባበር፣ ሱቃቸው ውስጥ የነበረውን ሸቀጣሸቀጥ ከመዝረፍም አልፈው በኩንታል የተቀመጠ እህላቸውን ኩንታሉን በሳንጃ በመበሳሳት እንዲፈስስ አድርገዋል።
ግፈኛው የፋሺስት ብልፅግና ገዳይ ጦር ግንቦት 6፣ 2024 በሳሲጋ ወረዳ፣ በdhአሳ ጃርሶ ቀበሌ ውስጥ ይኖር የነበረን ቄሮ ገረሙ ገቢሳን ወደ ቤተ እምነት እየሄደ ሳለ ሆሮ የሚባል ቦታ ላይ ገድለው ጥለውት መገኘቱን የአቢኦ ምንጮች አሳውቀዋል። ግዲያውን ያካሄዱትም አካል አምባገነኑ እና ፋሺስቱ አብይ አህመድ ነቀምቴ ይመጣል በሚል ሰበብ ለሰላም ጥበቃ የተሰማሩ ሲሆን በዚው ምክንያት የአካባቢውን ነዋሪዎችን ሲያሸብሩ እንደነበረ የዓይን እማኞች ለአቢኦ አክለው ገልፀዋል።
ጂማ ዞን
የማፍያው ብልፅግና ጦር የኦሮሞን ቤት በሌሊት ስብረው በመግባት እቤት ውስጥ ያገኙትን ህፃን፣ ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ወንድ ወይም ሴት ሳይሉ እየያዙ ወደ ጦር ካምፕ እያጋዙ ነው። ይህንንም በመመርኮዝ በዴዶ ወረዳ፣ አብዲ ጉዲና ቀበሌ በአንድ ምሽት ብቻ የኦሮሞን ቤቶች ሰብረው 22 ቄሮዎች መያዘቸውን የአቢኦ ምንጮች ገልፀዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎችም የብልፅግናው ጦር ቡድን ልጆቻቸውን የት እንዳደረሳቸው አለማወቃቸው እና ለሰብዓዊ መብታቸው የሚሟገትላቸው አካል በማጣታቸው ስጋት እንዳደረባቸው ለአቢኦ ገልፀዋል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
