ግንቦት 26፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የብልፅግና ቡድን የኦሮሞ ልጆችን በተለያዩ ቦታዎች ከፍላጎታቸው ውጪ በግድ ይዞ እነሱን በማይመለከታቸው ጦርነት አሳትፎ መማገድ የዘወትር ተግባሩ አድርጎታል።
ፋሺስት አብይ አህመድ የስልጣን ወንበሩን አጥብቆ ለመያዝ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆችን ህይወት እያስገበረ የቆየ እና ዛሬም እያስገበረ ያለ ሲሆን፣ በብልፅግና ቡድን ካምፕ ውስጥ ደግሞ የሀበሻ ልጆች በካምፑ በፋሺስት አብይ መሪነት የበላይነት ስላላቸው በኦሮሞ ልጆች ላይ በተደጋጋሚ ግድያ እና ስቃይ እያደረሱባቸው እንዳሉ ለኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እጃቸውን የሰጡ የኢምፓየሪቱ መከላከያ ሰራዊት አባሎች እየትናገሩ መቆየታቸው ይታወሳል።
በኦሮሞ ሰላማዊ ህዝብ ላይ የሚደረገው የጦር ወንጀል እና በብልፅግና ጦር ካምፖች ውስጥ ባለው ማንነት ላይ ያተኮረ ጥቃትንም ጨምሮ ማየትም ሆነ በዚህ እኩይ ተግባር ከተሰማራ ወራሪ ኃይል ጋር አባል ላለመሆን ከግዜ ወደ ግዜ የኦሮሞ ተወላጆች የስርዓቱን ካምፕ ረግጠው በመውጣት ለኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እጅ እየሰጡም ይገኛል። ይህንንም በመላው ኦሮሚያ እየተገበሩት ሲገኝ ጥቂት ዜናዎችን ከምዕራብ ሸገርና ከምዕራብ ወለጋ ዞኖች እዚሁ እናሰፍራለን።
የኦምፓየሪትዋን ገዳይ መከላከያ ጦር በመካድ የኦሮሞ ልጆች መንገዱም ቀንቶዋቸው ሊዋደቁለት ወደሚግባቸው ህዝባቸውና ወደ አለኝታ ጦራቸው የተቀላቀሉ ከጊዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ሄዶዋል። ወደ ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሚደርሱበትም ግዜ እንደ ኦሮሞ ባህል በየአካባቢው ሃላፊነት የተሰጣቸው አባሎችም ትልቅ አቀባበል ሲያደረጉላቸው አቢኦ በፎቶ ምስል እና በቪድዮም እያቀረበ ይገኛል።
በምዕራብ ሸገር ዞን አቡነ ግንደበረት ወረዳ
ሰኔ 12፣ 2024 ሶስት ወታደሮች ሶስት ድርብ ጠመንጃ እና 760 ጥይቶችንም ይዘው ወደሚገባቸው ትግል ደርሰው የያዙትንም የጦር መሳሪያ ለነፃነት ትግሉ ገቢ አድርገዋል።
በሰሜን ሸገር፣ ኩዩ ሞራ ዩዬ ጨወረዳ
በተመሳሳይ ቀን ማለትም ሰኔ 12፣ 2024 ሰባት ወታደሮች ስድስት AKM ጠመንጃ፣ አንድ ስናይፐር፣ 1203 ጥይቶች እንዲሁም ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው ወደ ጀግኖቹ በመድረስ ይዘውት የመጡትን የጦር መሳሪያዎች ለትግሉ ገቢ አድርገዋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ቆንዳላ ወረዳ
አንድ የብልፅግና ሰራዊት አባል አንድ የቱርክ ጠመንጃ ከነ ሙሉ ትጥቁ ይዞ ቤተስቡንና ጀግናውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ግንቦት 13፣ 2024 ተቀላቅሎ ይዞት የመጣውንም መሳሪያዎች ለነፃነት ትግሉ አበርክቷል።
በቄለም ወለጋ ዞን እና በሰሜን ኦሮሚያ በወሎ ዞን
የብልፅግናው ቡድን ጦር የኢምፓየሪትዋን መፈረካከስ ከዕለት ወደ እለት እዉን እየሆነ በመሄዱ ይህንን እውነታ መቀበል ያልፈለጉት የእአማራ አክራሪው ቡድን ወታደሮች በጦር ካምፓቸው ውስጥ ዘረኝነትን በማስፋፋት በኦሮሞ ወታደሮች ላይ ሁከት እና ግድያን መፈፀም ከጀመሩ ውለው አድረዋል። በዚሁ ሁኔታ የኦሮሞን ሰላማዊ ህዝብ መግደል ይቁም ያሉትን እና በማንነታቸው (ኦሮሙማ) የሚኮሩ የመሰላቸው ወታደሮች ላይ ተኩስ በመክፈት መገዳደሉንም ቀጥለዋል።
ቄለም ወለጋ ዞን፣ ጊዳሚ ወረዳ
ሰኔ 22፣ 2024 ዘረኝነትን በተላበሰ መንፈስ በተከፈተው ተኩስ አንድ የጦር አዛዥን ጨምሮ ከአራት በላይ ወታደሮች መገደላቸውን እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ደግሞ መቁሰላቸውን የአቢኦ ምንጮች ገልፀዋል።
ሰሜን ኦሮሚያ ወሎ ዞን፣ በከሚሴ ከተማ
በከሚሴ ከተማ 05 ቀበሌ ውስጥ ግንቦት 13፣ 2024 ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ 3:00 በቆየው የተኩስ ልውውጥ ኦሮሞ የሆኑ የኢምፓየሪትዋ የመከላከያ ሰራዊት አባል ሲገድሉ፣ የከተማው ፍርድ ቤት መርማሪ ፖሊስ ጌታቸው ጨመዳ የሚባለውን ደግሞ አቁስለውታል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
