• Fri. Mar 27th, 2026

የደቡብ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ በአበያና በቡሌ ሆራ ወረዳዎች የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻን በመመርኮዝ ጠላትን ማሩኝ የሚያሰኝ ቅጣት ሰጥቶ ሸኝቷል

Jul 16, 2024

ሐምሌ 16፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

አበያ ወረዳ

የደቡብ ዞን ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለዶ ዳዳ ቀበሌ ውስጥ ሐምሌ 8፣ ከጠዋቱ 3:00- እስከ 5:00 ሰዓት ባለው ግዜ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም የሚጠራው የማፍያው የአብይ አህመድ ጦር ቡድን ላይ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ ከ35 በላይ ሲገድል 23ቱን ደግሞ በማያገግም ቁስል ቀጥቷቸዋል።

በዚህ ውግያ የኦነሰ ጠላትን በጥይት ባሩድ ከማስከር ባሻገር የሚከተሉትን የጦር መሳሪያዎችንም፦ 

  • 12 AKM፣
  • 500 የAKM ጥይቶች፣
  • 635 የPKM ጥይቶች፣ 
  • 4 ቦምብ፣ 
  • 21 ሳጥን ጥይት እና 
  • 200 የPKM ጆሮሮ

ከጀርባቸው ላይ በመፍታት ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ገቢ አድርጓል።

ቡሌ ሆራ ወረዳ

በጨሪ ሰጰሊሳ ቀበሌ

ሐምሌ 4፣ 2024 ጀግናው የደቡብ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻን ምክንያት በማድረግ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ በፋሺስት የብልፅግና ጦር በጨሪ ሰጰሊሳ ቀበሌ ውስጥ የወሰደ ሲሆን ሙት እና ቁስለኞችም አድርጎ ሸኝቷል። ከዚህም ባሻገር ሁለት AKM ጠመንጃዎች ከነ ሙሉ ትጥቁ ከጠላት ጀርባ ላይ በመፍታት ለኦሮሞ ነፃነት ትግል አበርክቶዋል።

ሀሮ ባርታ ቀበሌ

የደቡብ ዞን አምበሳው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሰኔ 29፣ 2024 ሌሊት ወደ ሀሮ  በወሰደው እርምጃ አመርቂ ድል አስመዝግቧል።

በዚሁ በፋሽስት የኢትዮጵያ ጦር ላይ በወሰደው እርምጃ ብዙዎቹን በሙት እና በቁስለኛነት በመቅጣት አንድ AKM ጠመንጃ ከላያቸው ላይ በመፍታት ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ዓላማ ገቢ አድርጓል።

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading