ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሞያሌ ድንበር ከተማ፣ ከኢትዮጵያ ድንበር አቋርጠው በመጡ ታጣቂዎች፤ በኦሮሞ ተወላጆች እና በውጭ ሐገር ዜጎች ላይ ያነጣጠረ የተኩስ፣ የቃጠሎ እና የአፈና ወንጀሎች ተከስተዋል። ነሐሴ 12፣ 2024 በተፈፀመው ጥቃት አብዛኛዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት አጥቂዎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የኬንያ ፖሊስ አረጋግጧል። ንጹሃን ዜጎችን ኢላማ ያደረገው አሰቃቂ ጥቃት፣ በተጎዱት ሰዎች ላይ ወንጀል መፈፀሙ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ አደጋ አለው። እንዲህ ዓይነቱ ጠብ አጫሪ ባህርይ የዓለም አቀፍ ህግጋቶችን በግልጽ ከመጣስም በላይ በሁለቱም የድንበር አካባቢዎች ለሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች ደህንነት ቀጥተኛ አደጋ ነው።
የወንጀል ምርመራው አሁንም በመካሄድ ላይ ባለበት ወቅት፣ ከመጀመሪያዎቹ የስልጣን ቀናቶቹ ጀምሮ አለመረጋጋትን ወደ ውጭ በመላክ እና በመጋበዝ የተካነው አራት ኪሎው አምባገነን መንግስት ተቀዳሚ ተጠርጣሪ ነው። በአራት አመታት ውስጥ ብቻ አብይ አህመድ የውጭ ኃይሎችን በመጋበዝ የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል፣ የጎርቤት አገሮች ሰራዊትን ጋብዞ የሉዓላዊት ሐገርን ድንበር እንዲወርሩ አድርጓል፣ የውጭ ኃይል ጥቅም አስከባሪ እና ወኪል በመሆን ሱዳን እንዳትረጋጋ አድርጓል፣ ከሱማሌላንድ ጋር ባደረገው የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት፣ በሶማሊያ ላይ እሳት አቀጣጥሏል፣ እና ከጅቡቲ ጋርም የሻከረ ግንኙነት ዉስጥ ገብቷል። አሁን ደግሞ በአካባቢው ብቸኛዋ እና የተረጋጋች አገር ወደሆነችው ኬንያ ያነጣጠረ ይመስላል።
በኢትዮጵያ መንግስት የሚመራው ድንበር ዘለል ዘመቻ በሚመስል መልኩ የታጠቁ ሚሊሻዎቹን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ያሰማራው፣ በኬንያ የሚገኙ ኦሮሞዎችን ለማጥቃት እና የውጭ ዜጎችን ለማፈን ነው። የአብይ መንግስት ይህንን ወንጀል ሊፈፅም ካበራታታው በርካታ ምክንያቶች መካከል፦
1) እንደለመደው የኦነግ-የኦነሰን ስም ለማጠልሸት፣
2) በኬንያ የሚኖሩ፣ የኦሮሞን ነፃነት ትግልን የሚደግፉ የኦሮሞ ማህበረሰብን ለማሸበር፤ እና
3) በቅርቡ ኬንያ ኢትዮጵያን ተክታ እንደ የቀጠናው ወኪል ስለሆነች ኬንያ ዉስጥ አለመረጋጋት ለመፍጠር ነው። ስሜታዊው ጠ/ሚንስቴር በትልቅና በትንሽ ጉዳዮች ከኬንያ አመራሮች ጋር እየተፎካከረ ይገኛል። የኬንያ ጠንካራና ቋሚ መረጋጋት፣ የህዝብ ተቃውሞውን በጥበብ፣ ብቃት እና ሰፊ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ አያያዝ፣ የአብይ አህመድ አገዛዝ ማንነት እና በቀጠናው ያለውን ሚና ያመላክታል። በእነዚህ ወንጀሎች ላይ በተደረገው ምርመራ መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ነፃ ቢወጡም እንኳ፣ ይህ ድርጊት ቢያንስ ቢያንስ የኢትዮጵያ ግዛት በጎረቤት አገሮች ላይ አሰቃቂ ጥቃቶችን ለማድረስ መንደርደሪያ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን ያሳያል።
ከተጎጂዎች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር፣ እንዲሁም ሰላም እና ደህንነትን ወደነበረበት ለመመለስ በቁርጠኝነት ለመስራት የሚጥሩ አካላትን እንደግፋለን። በመጨረሻም ለኬንያ ባለስልጣናት እና በአካባቢው ለሚገኙ ዓለም አቀፍ አጋሮች የቀጠናውን መረጋጋት በሚያውኩ ኃይላት ላይ በሚደረጉት ማንኛውም ምርመራ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።
የኦነግ – የኦነሰ ከፍተኛ አዛዥ
ነሐሴ 16፣ 2024
