• Mon. Nov 9th, 2026

በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በቡኖ በደሌ እና በምዕራብ ሸገር ዞኖች የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን ጦር የኦሮሞን ህዝብ ማሰር፣ ማሰቃየት፣ በኤሌክትሪክ ሽቦም ሳይቀር ማቃጠል እና መግደል ቀጥሏል

Aug 31, 2024

ነሐሴ 28፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)  

የብልፅግናው ቡድን ጦር የኦሮሞን ህዝብ ማሰር፣ ማስቃየት እና መግደልን አጠናክሮ ቀጥሎዋል። ለዚህም ምክንያት የሚሰጠው ከኦነሰ ጋር፥ ግንኙነት አላችሁ፣ ትረዳላችሁ እንዲሁም ወታደሮቻችን ክደው ወደ ኦነሰ እንዲገቡ የምታመቻቹት እናንተ ናችሁ በሚል የሃሰት ውንጀላ መሆኑን የሶስቱም ዞን ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።  

ምሥራቅ ሐረርጌ

ሐምሌ 27፣ 2024 በበደምኖ ወረዳ የብልፅግናው ጦር ቡድን ቄሮ ከማል ሀሰንን ወደ እስር ቤት ካስገቡት በኋላ “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትደግፋለህ!” በሚል ወንጅለው እንዲያምንም ሌላው የማሰቃያ ስልታቸው አላረካ ብሎዋቸው በኤሌክትሪክ ሽቦም ሰውነቱን አቃጥለውታል።

ይህ ቄሮ በምንም ዓይነት ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ የሌለው ሲሆን የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር ቡድን በኃይል ለማሳመን እንዲህ አሰቃቂ ወንጀል ፈፅመውበታል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልፀዋል።

ቡኖ በደሌ ዞን 

በጮራ ወረዳ “ከ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አላችሁ።” በማለት የብልፅግናው ጦር ቡድን ሰላማዊውን የኦሮሞ ህብረተሰብን ማሰር እና መዝረፍ አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ይኸውም ሐምሌ 25፣ 2024 በርካታ ግለሰቦችን ይዘው ወደ ወረዳው ፖሊስ ጣቢያ አስረዋል። ከታሰሩትም ውስጥ ስማቸውን አቢኦ ያገኘው፦

  1. ብራኑ ጫሊ
  2. ፌdhaሳ ሙለታ
  3. አብዲ ያደታ እና
  4. ዋቅጋሪ አብዲሳ ናቸው። 

በወረዳው ፖሊስ ጣቢያም ክፋኛ ሰቃይ ውስጥ መሆናቸው እና በወረዳውም ብዙ ሰዎች ታፍነው እየተወሰዱ ሲሆን ቤተሰብ በፍለጋ እየተሰቃየ መሆኑንም የወረዳው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።

በምዕራብ ሸገር ዞን

ከዚህም ሌላ በምዕራብ ሸገር ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ዘረፋ እስራት እና ግድያ እየተካሄደ ይገኛል። ይህንንም ወንጀል የሚፈፅሙት “የኦሮሞ ነፃነት ስራዊትን ለማሰስ” በሚል የፋሺስት ብልፅግና ስርዓት ያሰማራቸው የጦር ቡድን ነው። 

በጮቢ ወረዳ የብልፅግናን ሰራዊት በመክዳት ወደ ኦነሰ የሚቀላቀሉትም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በመሄዱም አንድ ለጊዜው ስሙን ለማግኘት ያልቻልነውን ግለሰብ “አንተ ነህ የኛን ሰራዊት አባሎች እንዲክዱ ያመቻቸኸው” ብለው በጥይት ደብድበው ገድለውታል።

የኦሮሞ ጉበሬዎችን ለምን አርሳችሁ እራሳችሁን እና ቤተስቦቻችሁን ትመግባላችሁ? ለምን ለመሬታችሁ እንክብካቤ ታደርጋላችሁ? ለምን እራሳችሁን እና አብራችሁ ከምትኖሩት ማህበረሰብ ጋር በመተባበር እና መከባበር ትኖራላችሁ በማልት ከዚህ በታች ስማቸው ይተጠቀሱ ገበሬዎችን፦

  1. ሌቺሳ ቦኮኔ እና
  2. አራሬ ሜሲሳ አስረው እያሰቃዩዋቸው ይገኛሉ።

ቤተሰቦቻቸውም በጣም ከባድ ችግር ላይ መሆናቸውን እና የአካባቢው ነዋሪዎችም ለራሳቸው ደህንነት እንደሚያሳስባቸው ለአቢኦ ገልፀዋል።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ለማስገደል መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

#ጨቋኙ_ኃይል_በኦነሰ_ኃይል_ይገረሰሳል!

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

Leave a Reply